ዘዳግም 18:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)22 ነቢዩ በጌታ ስም የተናገረው ካልተፈጸመ ወይም እውነት ሆኖ ካልተገለጸ፥ መልእክቱ ጌታ የተናገረው አይደለም። ያ ነቢይ በድፍረት ተናግሮታልና እርሱን አትፍራው።” ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም22 ነቢዩ በእግዚአብሔር ስም የተናገረው ካልተፈጸመ ወይም እውነት ሆኖ ካልተገኘ፣ መልእክቱ እግዚአብሔር የተናገረው አይደለም። ያ ነቢይ በድፍረት ተናግሮታልና እርሱን አትፍራው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም22 አንድ ነቢይ በእግዚአብሔር ስም ትንቢት ተናግሮ ቃሉ ሳይፈጸም ቢቀር ያ ትንቢት ነቢዩ በግምት የተናገረው ነው እንጂ ከእግዚአብሔር ተሰጥቶት የተናገረው ቃል ስላልሆነ ልትፈራው አይገባም። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)22 ያ ነቢይ በእግዚአብሔር ስም ከተናገረው ሁሉ ቃሉ ባይደርስ፤ እንደ ተናገረውም ባይሆን እግዚአብሔር ያን ቃል አልተናገረውም፤ ነቢዩ በሐሰት ተናግሮታልና አትስማው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)22 ነቢዩ በእግዚአብሔር ስም በተናገረ ጊዜ የተናገረው ነገር ባይሆን ባይመጣም፥ ያ ነገር እግዚአብሔር ያልተናገረው ነው፤ ነቢዩ በድፍረቱ ተናግሮታል እርሱን አትፍራው። ምዕራፉን ተመልከት |