ስለዚህም ነው ስምህን እንድንጠራ አንተን መፍራት በልባችን ውስጥ ያሳደርኸው፤ በስደት ላይ ሆነን እናመስግንሃለን፥ በአንተ ላይ የበደሉትን የአባቶቻችንን ክፋት ሁሉ ከልባችን አርቀናልና።
ስለዚህም ስምህን እንጠራ ዘንድ፥ ባስማረክኸንም ቦታ እናመሰግንህ ዘንድ መፈራትህን በልቡናችን አሳደርህ። በፊትህ የበደሉ የአባቶቻችንን ክፋት ሁሉ ከልባችን አርቀናልና።