እኛ በጌታ በአምላካችን ላይ ኃጢአትን ሰርተናልና፥ እስከዚችም ቀን ድረስ የጌታ መዓቱና ቁጣው ከኛ አልራቀምና ወደ ጌታ ወደ አምላካችን ጸልዩልን።
አምላካችንን በድለናልና፤ የእግዚአብሔርም መዓቱ መቅሠፍቱም እስከዚች ቀን ድረስ ከእኛ አልተመለሰችምና ለእኛም ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ጸልዩልን።