ሐዋርያት ሥራ 2:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህም ድምፅ በሆነ ጊዜ ሕዝብ ሁሉ ተሰበሰቡ፤ እያንዳንዱም በገዛ ቋንቋው ሲናገሩ ይሰማ ስለ ነበር የሚሉትን አጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህን ድምፅ ሲሰሙ፣ ብዙ ሕዝብ በአንድነት ተሰበሰቡ፤ እያንዳንዱም ሰው፣ ሰዎቹ በገዛ ቋንቋው ሲናገሩ በመስማቱ ግራ ተጋባ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህንንም ድምፅ በሰሙ ጊዜ ብዙ ሰዎች ተሰበሰቡ፤ በየቋንቋቸውም ሲናገሩ ስለ ሰሙአቸው ተደነቁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህንም ቃል ሲናገሩ ሰምተው ሁሉም ደንግጠው ተሰበሰቡ፤ ሁሉም በየሀገራቸው ቋንቋ ሲናገሩ ሰምተዋቸዋልና የሚሉትን አጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህም ድምፅ በሆነ ጊዜ ሕዝብ ሁሉ ተሰበሰቡ፥ እያንዳንዱም በገዛ ቋንቋው ሲናገሩ ይሰማ ስለ ነበር የሚሉትን አጡ። |