ሐዋርያት ሥራ 19:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እንደዚህ ከሆነስ በምን ተጠመቃችሁ?” አላቸው። እነርሱም “በዮሐንስ ጥምቀት፤” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጳውሎስም፣ “ታዲያ፣ በምን ተጠመቃችሁ?” አላቸው። እነርሱም፣ “የዮሐንስን ጥምቀት” አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጳውሎስም “ታዲያ፥ ምን ዐይነት ጥምቀት ነው የተጠመቃችሁት?” አላቸው። እነርሱም “የዮሐንስን ጥምቀት ነው” አሉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም፥ “እንኪያ በምን ተጠመቃችሁ?” አላቸው፤ እነርሱም፥ “በዮሐንስ ጥምቀት” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንኪያ በምን ተጠመቃችሁ? አላቸው። እነርሱም፦ በዮሐንስ ጥምቀት አሉት። |
አይሁድ ብንሆን የግሪክ ሰዎችም ብንሆን ባርያዎችም ብንሆን ጨዋዎችም ብንሆን እኛ ሁላችን በአንድ መንፈስ አንድ አካል እንድንሆን ተጠምቀናልና። ሁላችንም አንዱን መንፈስ ጠጥተናል።