3 ዮሐንስ 1:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወዳጄ ሆይ! በመንፈስ እንዳደግህ ሁሉ፥ በነገር ሁሉ እንዲሳካልህና በመልካም ጤንነት እንድትኖር እጸልያለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወዳጅ ሆይ፤ ነፍስህ በመልካም ሁኔታ ላይ እንዳለች ሁሉ መልካም ጤንነት እንዲኖርህና በነገር ሁሉ እንዲሳካልህ እጸልያለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወዳጄ ሆይ! ኑሮህ ሁሉ እንዲሳካልህ፥ ጤንነት እንዲኖርህና እንዲሁም የመንፈስ እርካታ እንድታገኝ እመኝልሃለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወዳጅ ሆይ! ነፍስህ እንደሚከናወን፥ በነገር ሁሉ እንዲከናወንልህና ጤና እንዲኖርህ እጸልያለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወዳጅ ሆይ፥ ነፍስህ እንደሚከናወን፥ በነገር ሁሉ እንዲከናወንልህና ጤና እንዲኖርህ እጸልያለሁ። |
በእርግጥ በጠና ታሞ ለሞት ተቃርቦ ነበርና፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ማረው፤ እግዚአብሔርም እንዲህ ያደረገው ለእርሱ ብቻ ሳይሆን ኀዘን በኀዘን ላይ እንዳይደራረብብኝ ለእኔም ደግሞ ነው።
ወንድሞች ሆይ! እምነታችሁ እጅግ አድጎአልና፥ የእናንተም የእያንዳንዳችሁ ሁሉ ፍቅር ለእርስ በርሳችሁ በዝቶአልና፥ ሁልጊዜ ስለ እናንተ እግዚአብሔርን እንደሚገባ ልናመሰግን ግዴታ አለብን፤
በጌታ የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ! እኛ ግን ስለ እናንተ እግዚአብሔርን ሁልጊዜ ልናመሰግን ይገባናል፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ከመጀመሪያው አንሥቶ በመንፈስ በመቀደስና በእውነት በማመን እንድትድኑ መርጦአችኋልና፤
ከሁሉም በላይ ወንድሞቼ ሆይ! በሰማይ ወይም በምድር ወይም በማናቸውም ነገር ቢሆን አትማሉ፤ ነገር ግን ከፍርድ በታች እንዳትወድቁ፥ ነገራችሁ “አዎ” ቢሆን አዎ ይሁን፤ “አይደለም” ቢሆን አይደለም ይሁን።
“መከራህንና ድህነትህን አውቃለሁ፤ ነገር ግን ሀብታም ነህ፤ አይሁድ ሳይሆኑ ‘አይሁድ ነን’ የሚሉት፥ ይልቁንም የሰይጣንም ማኅበር የሆኑት፥ የሚሳደቡትን ስድብ አውቃለሁ።