2 ጢሞቴዎስ 3:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፍቅር የሌላቸው፥ ዕርቅን የማይሰሙ፥ ሐሜተኞች፥ ራሳቸውን የማይቈጣጠሩ፥ ጨካኞች፥ መልካም የሆነውን የማይወዱ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፍቅር የሌላቸው፣ ለዕርቅ የማይሸነፉ፣ ሐሜተኞች፣ ራሳቸውን የማይገዙ፣ ጨካኞች፣ መልካም የሆነውን የማይወድዱ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፍቅር የሌላቸው፥ ይቅርታ የማያደርጉ፥ የሰው ስም የሚያጠፉ፥ ራሳቸውን የማይቈጣጠሩ፥ ጨካኞች፥ መልካም የሆነውን ነገር የሚጠሉ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፍቅር የሌላቸው፥ ዕርቅን የማይሰሙ፥ ሐሜተኞች፥ ራሳቸውን የማይገዙ፥ ጨካኞች፥ መልካም የሆነውን የማይወዱ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቅድስና የሌላቸው፥ ፍቅር የሌላቸው፥ ዕርቅን የማይሰሙ፥ ሐሜተኞች፥ ራሳቸውን የማይገዙ፥ ጨካኞች፥ መልካም የሆነውን የማይወዱ፥ |
የአስጨናቂዎችሽ ልጆች አንገታቸውን ደፍተው ወደ አንቺ ይመጣሉ፤ የናቁሽም ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ፤ የጌታም ከተማ፥ የእስራኤል ቅዱስ የሆንሽ ጽዮን ይሉሻል።
ለጸሎት ለመትጋት ተስማምታችሁ ለተወሰነ ጊዜ ካልሆነ በቀር፥ እርስ በርሳችሁ አትከላከሉ፤ እንዲሁም ራሳችሁን ስለ አለመግዛት ሰይጣን እንዳይፈታተናችሁ አብራችሁ ሁኑ።
እንዲሁም በዕድሜ የገፉ ሴቶች በመልካም ጠባያቸው የተቀደሱ፥ የማያሙ፥ ለብዙ ወይን ጠጅ ያልተገዙ፥ በጎ የሆነውን ነገር የሚያስተምሩ እንዲሆኑ ንገራቸው፤