2 ሳሙኤል 9:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ጺባ ንጉሡን፥ “ጌታዬ ንጉሥ፥ አገልጋዩን ያዘዘውን ሁሉ፥ አገልጋይህ ይፈጽመዋል” አለው። ስለዚህም መፊቦሼት እንደ አንዱ ሆኖ ከዳዊት ማእድ ይበላ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ሲባ ንጉሡን፣ “ጌታዬ ንጉሥ፣ አገልጋዩን ያዘዘውን ሁሉ፣ አገልጋይህም ይፈጽመዋል” አለው። ስለዚህም ሜምፊቦስቴ ከንጉሡ ልጆች እንደ አንዱ ሆኖ ከዳዊት ማእድ ይበላ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጺባም “ንጉሥ ሆይ! እኔ አገልጋይህ አንተ ያዘዝከውን ሁሉ እፈጽማለሁ” ሲል መለሰ። በዚህ ዐይነት መፊቦሼት ከንጉሡ ልጆች እንደ አንዱ ተቈጥሮ በንጉሥ ገበታ እየቀረበ ይመገብ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሲባም ንጉሡን፥ “ጌታዬ ንጉሡ አገልጋዩን እንዳዘዘ እንዲሁ አገልጋይህ ያደርጋል” አለው። ሜምፌቡስቴም ከንጉሡ ልጆች እንደ አንዱ ከዳዊት ገበታ ይበላ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሲባም ንጉሡን፦ ጌታዬ ንጉሡ ባሪያውን እንዳዘዘ እንዲሁ ባሪያህ ያደርጋል አለው። ሜምፊቦስቴም ከንጉሡ ልጆች እንደ አንዱ ከዳዊት ገበታ ይበላ ነበር። |
አንተ፥ ልጆችህና አገልጋዮችህ የጌታችሁ የልጅ ልጅ የሚበላውን እንዲያገኝ መሬቱን እረሱለት፥ ምርቱንም አግቡለት። የጌታህ የልጅ ልጅ መፊቦሼት ግን ምንጊዜም ከማእዴ ይበላል።” በዚያን ጊዜ ጺባ ዐሥራ አምስት ወንዶች ልጆችና ሃያ አገልጋዮች ነበሩት።