2 ሳሙኤል 19:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)24 ስለዚህ ንጉሡ ሺምዒን፥ “አትሞትም” አለው፤ ይህንንም ንጉሡ በመሐላ አጸናለት። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም24 የሳኦል ልጅ ሜምፊቦስቴም ንጉሡን ለመቀበል ወረደ። ንጉሡ ከተሰደደበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ተመለሰበት ዕለት ድረስ ለእግሩ ተገቢውን ጥንቃቄ አላደረገም፤ ጢሙን አልተላጨም፤ ልብሱንም አላጠበም ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም24 ከዚህ በኋላ የሳኦል የልጅ ልጅ መፊቦሼት ንጉሡን ለመቀበል ወረደ፤ ንጉሡ ከኢየሩሳሌም ከወጣበት ጊዜ አንሥቶ አሁን በድል አድራጊነት እስከ ተመለሰበት ጊዜ ድረስ መፊቦሼት እግሩን አልታጠበም፤ ጢሙን አልተላጨም፤ ልብሱንም አላጠበም። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)24 የሳኦልም የልጅ ልጅ ሜምፌቡስቴ ንጉሡን ሊቀበል ወረደ፤ ንጉሡም ከሄደበት ቀን ጀምሮ በሰላም እስከ ተመለሰበት ቀን ድረስ እግሩን አላነጻም፤ ጥፍሩንም አልቈረጠም፤ ጢሙንም አልላጨም፤ ልብሱንም አላጠበም ነበር። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)24 የሳኦልም ልጅ ሜምፊቦስቴ ንጉሡን ሊቀበል ወረደ፥ ንጉሡም ከሄደ ጀምሮ በደኅና እስከ ተመለሰበት ቀን ድረስ እግሩን አልጠገነም፥ ጢሙንም አልቆረጠም፥ ልብሱንም አላጠበም ነበር። ምዕራፉን ተመልከት |