2 ሳሙኤል 9:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 አንተ፥ ልጆችህና አገልጋዮችህ የጌታችሁ የልጅ ልጅ የሚበላውን እንዲያገኝ መሬቱን እረሱለት፥ ምርቱንም አግቡለት። የጌታህ የልጅ ልጅ መፊቦሼት ግን ምንጊዜም ከማእዴ ይበላል።” በዚያን ጊዜ ጺባ ዐሥራ አምስት ወንዶች ልጆችና ሃያ አገልጋዮች ነበሩት። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም10 አንተ፣ ልጆችህና አገልጋዮችህ የጌታችሁ የልጅ ልጅ የሚበላውን እንዲያገኝ መሬቱን ዕረሱለት፣ ምርቱንም አግቡለት። የጌታህ የልጅ ልጅ ሜምፊቦስቴ ግን ምን ጊዜም ከማእዴ ይበላል።” በዚያ ጊዜ ሲባ ዐሥራ ዐምስት ወንዶች ልጆችና ሃያ አገልጋዮች ነበሩት። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 አንተ፥ ወንዶች ልጆችህና አገልጋዮችህ ለጌታህ ለሳኦል ቤተሰብ ምድሪቱን አርሳችሁ ምግብ ይሆናቸው ዘንድ መከሩን አገቡላቸው፤ የጌታህ የልጅ ልጅ መፊቦሼት ግን ዘወትር በገበታዬ የሚቀርብ ተመጋቢ ይሆናል፤” ጺባ ዐሥራ አምስት ወንዶች ልጆችና ኻያ አገልጋዮች ነበሩት። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 አንተና ልጆችህ፥ ሎሌዎችህም ምድሩን እረሱለት፤ ለጌታህም ልጅ እንጀራ ይሆነው ዘንድ ፍሬውን አግቡ፤ እናንተም ትመግቡታላችሁ፤የጌታህ ልጅ ሜምፌቡስቴ ግን ሁልጊዜ ከገበታዬ ይበላል” አለው። ለሲባም ዐሥራ አምስት ልጆችና ሃያ አገልጋዮች ነበሩት። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 አንተና ልጆችህ ሎሌዎችህም ምድሩን እረሱለት፥ ለጌታህም ልጅ እንጀራ ይሆነው ዘንድ ፍሬውን አግባ፥ የጌታህ ልጅ ሜምፊቦስቴ ግን ሁልጊዜ ከገበታዬ ይበላል አለው። ለሲባም አሥራ አምስት ልጆችና ሀያ ባሪያዎች ነበሩት። ምዕራፉን ተመልከት |