በዚያን ጊዜም የዳዊት አገልጋዮችና ኢዮአብ ብዙ ምርኮ ይዘው ከዘመቻ ተመለሱ። አበኔር ግን ዳዊት በሰላም አሰናብቶት ስለ ሄደ፥ በኬብሮን አልነበረም።
2 ሳሙኤል 3:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢዮአብና አብሮት የነበረው ሠራዊት ሁሉ እዚያ እንደ ደረሱ፥ “የኔር ልጅ አበኔር ወደ ንጉሡ መጣ፥ አሰናበተውም እርሱም በሰላም ሄደ” ብለው ለኢዮአብ ነገሩት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢዮአብና ዐብሮት የነበረው ሰራዊት ሁሉ እዚያ እንደ ደረሱ፣ የኔር ልጅ አበኔር ወደ ንጉሡ መምጣቱን፣ ንጉሡ እንዳሰናበተውና እርሱም በሰላም እንደ ሄደ፣ ኢዮአብ ሰማ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዮአብና ተከታዮቹ በደረሱም ጊዜ የኔር ልጅ አበኔር ወደ ንጉሥ ዳዊት መጥቶ ንጉሡ አበኔርን በሰላም እንዳሰናበተው ለኢዮአብ ነገሩት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዮአብና ከእርሱም ጋር የነበረ ጭፍራ ሁሉ በመጡ ጊዜ፥ “የኔር ልጅ አበኔር ወደ ንጉሥ መጣ፤ አሰናበተውም፤ በሰላምም ሄደ” ብለው ሰዎች ለኢዮአብ ነገሩት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዮአብና ከእርሱም ጋር የነበረ ጭፍራ ሁሉ በመጡ ጊዜ፦ የኔር ልጅ አበኔር ወደ ንጉሥ መጣ፥ አሰናበተውም በደኅናውም ሄደ ብለው ሰዎች ለኢዮአብ ነገሩት። |
በዚያን ጊዜም የዳዊት አገልጋዮችና ኢዮአብ ብዙ ምርኮ ይዘው ከዘመቻ ተመለሱ። አበኔር ግን ዳዊት በሰላም አሰናብቶት ስለ ሄደ፥ በኬብሮን አልነበረም።