2 ሳሙኤል 22:40 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለጦርነት ኃይልን ታስታጥቀኛለህ፥ በላዬ የቆሙትን በበታቼ ታስገዛለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለጦርነት ኀይልን አስታጠቅኸኝ፣ ተቃዋሚዎቼንም ከእግሬ ሥር አንበረከክሃቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለጦርነት ኀይልን ትሰጠኛለህ፤ በጠላቶቼም ላይ ድልን ታጐናጽፈኛለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጦርነትም ጊዜ በኀይል ታጸናኛለህ፤ በላዬ የቆሙትንም በበታቼ ታስገዛቸዋለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለሰልፍም ኃይልን ታስታጥቀኛለህ፥ በላዬ የቆሙትን በበታቼ ታስገዛቸዋለህ። |
የአስጨናቂዎችሽ ልጆች አንገታቸውን ደፍተው ወደ አንቺ ይመጣሉ፤ የናቁሽም ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ፤ የጌታም ከተማ፥ የእስራኤል ቅዱስ የሆንሽ ጽዮን ይሉሻል።
“መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል ታርደሃልና፤ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ፥ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፤ በምድርም ላይ ይነግሣሉ፤” እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ።
ስለዚህ ዳዊትና ሰዎቹ ወደ ቅዒላ ሄደው፥ ፍልስጥኤማውያንን ወጉ፤ እንስሶቻቸውን ማርከው ወሰዱ፤ በፍልስጥኤማውያን ላይ ከባድ ጉዳት አደረሱ፤ ዳዊትም የቅዒላን ሕዝብ ታደገ።