1 ሳሙኤል 23:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 ስለዚህ ዳዊትና ሰዎቹ ወደ ቅዒላ ሄደው፥ ፍልስጥኤማውያንን ወጉ፤ እንስሶቻቸውን ማርከው ወሰዱ፤ በፍልስጥኤማውያን ላይ ከባድ ጉዳት አደረሱ፤ ዳዊትም የቅዒላን ሕዝብ ታደገ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም5 ስለዚህ ዳዊትና ሰዎቹ ወደ ቅዒላ ሄደው፣ ፍልስጥኤማውያንን ወጉ፤ እንስሶቻቸውን ማርከው ወሰዱ፤ በፍልስጥኤማውያን ላይ ከባድ ጕዳት አደረሱ፤ ዳዊትም የቅዒላን ሕዝብ ታደገ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 ስለዚህም ዳዊትና ተከታዮቹ ወደ ቀዒላ ሄደው በፍልስጥኤማውያን ላይ አደጋ ጣሉባቸው፤ ከእነርሱም ብዙዎቹን ገድለው የከብትና የበግ መንጋዎቻቸውን ዘርፈው ወሰዱ፤ በዚህም ዐይነት ዳዊት ከተማይቱን ከጥፋት አዳናት። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 ዳዊትና ሰዎቹም ወደ ቂአላ ሄዱ፤ ከፍልስጥኤማውያንም ጋር ተዋጉ፤ እነርሱም ከፊቱ ሸሹ፤ እንስሶቻቸውንም ማረኩ፤ በታላቅም አገዳደል ገደሉአቸው። ዳዊትም በቂአላ የሚኖሩትን አዳነ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 ዳዊትና ሰዎቹም ወደ ቅዒላ ሄዱ፥ ከፍልስጥኤማውያንም ጋር ተዋጉ፥ እንስሶቻቸውንም ማረኩ፥ በታላቅም አገዳደል ገደሉአቸው። ዳዊትም በቅዒላ የሚኖሩትን አዳነ። ምዕራፉን ተመልከት |