2 ሳሙኤል 19:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መፊቦሼትም ንጉሡን፥ “ንጉሥ ጌታዬ እንኳን በደኅና ተመለሰ እንጂ፥ እርሱ ሁሉንም ይውሰደው” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም ገለዓዳዊው ቤርዜሊ ከሮግሊም ወረደ፤ ንጉሡን ለመሸኘትም ዐብሮት ዮርዳኖስን ተሻገረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ገለዓዳዊው ባርዚላይ ንጉሡን አጅቦ የዮርዳኖስን ወንዝ ለመሻገር ከሮገሊም መጣ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ገለዓዳዊውም ቤርዜሊ ከሮግሊም ወረደ፤ በዮርዳኖስም ሊሸኘው ከንጉሡ ጋር ዮርዳኖስን ተሻገረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ገለዓዳዊውም ቤርዜሊ ከሮግሊም ወረደ፥ ሊሸኘውም ከንጉሡ ጋር ዮርዳኖስን ተሻገረ። |
“ከወንድምህ ከአቤሴሎም ፊት በሸሸሁ ጊዜ የቸርነት ሥራ ስላደረጉልኝ ለገለዓዳዊው ለባርዚላይ ልጆች ግን መልካም ነገር በማድረግ ተንከባከባቸው፤ በማዕድህም ከሚመገቡት መካከል ይሁኑ።
ከካህናቱም የሐባያ ልጆች፥ የሃቆጽ ልጆች፥ የባርዚላይ ልጆች እሱም ከገለዓዳዊው የባርዚላይ ሴቶች ልጆች ሚስት ያገባ፥ በስማቸውም የተጠራ ነው።