Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 19:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 ገለዓዳዊው ባርዚላይ ንጉሡን አጅቦ የዮርዳኖስን ወንዝ ለመሻገር ከሮገሊም መጣ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 እንዲሁም ገለዓዳዊው ቤርዜሊ ከሮግሊም ወረደ፤ ንጉሡን ለመሸኘትም ዐብሮት ዮርዳኖስን ተሻገረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 መፊቦሼትም ንጉሡን፥ “ንጉሥ ጌታዬ እንኳን በደኅና ተመለሰ እንጂ፥ እርሱ ሁሉንም ይውሰደው” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 ገለ​ዓ​ዳ​ዊ​ውም ቤር​ዜሊ ከሮ​ግ​ሊም ወረደ፤ በዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም ሊሸ​ኘው ከን​ጉሡ ጋር ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ገረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 ገለዓዳዊውም ቤርዜሊ ከሮግሊም ወረደ፥ ሊሸኘውም ከንጉሡ ጋር ዮርዳኖስን ተሻገረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 19:31
5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“ከወንድምህ ከአቤሴሎም ፊት በሸሸሁ ጊዜ የቸርነት ሥራ ስላደረጉልኝ ለገለዓዳዊው ለባርዚላይ ልጆች ግን መልካም ነገር በማድረግ ተንከባከባቸው፤ በማዕድህም ከሚመገቡት መካከል ይሁኑ።


ከዚህ የሚከተሉት የካህናት ጐሣዎች የቀድሞ አባቶቻቸውን የትውልድ ሐረግ ለማረጋገጥ አልቻሉም፤ እነርሱም ሖባያ፥ ሀቆጽና ባርዚላይ ናቸው፤ የካህን ወገን የሆነው የባርዚላይ የቀድሞ አባት የገለዓድ ተወላጅ ከነበረው ከባርዚላይ ወገን አንዲት ሴት አግብቶ ነበር፤ ከዚህም የተነሣ የዐማቱን ጐሣ ስም ወርሶ ይኖር ነበር፤ የቀድሞ አባቶቻቸውንም የትውልድ ሐረግ ለማረጋገጥ ካለመቻላቸው የተነሣ፥ በክህነት ለማገልገል አልተፈቀደላቸውም።


ከዚህ የሚከተሉት የካህናት ጐሣዎች ሐባያ፥ ሀቆጽና ባርዚላይ የቀድሞ አባቶች እነማን እንደ ነበሩ ካለማወቃቸውም የተነሣ ካህናት ሆነው ለማገልገል ተቀባይነት አላገኙም። (ባርዚላይ ከገለዓዳዊው የባርዚላይ ልጆች አንድዋን አግብቶ በዚሁ ስም ይጠራ ነበር)።


መፊቦሼትም “ንጉሥ ሆይ! ሁሉንም ሀብት ጺባ ይውሰደው፤ ለእኔ አንተ በሰላም ወደ ቤትህ መመለስህ ብቻ ይበቃኛል” አለ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች