አሁንም አገልጋይህ፤ ‘ንጉሥ ጌታዬ በጎውንና ክፉውን በመለየት እንደ እግዚአብሔር መልአክ ስለሆነ፥ የጌታዬ የንጉሡ ቃል ያጽናናኝ፤ ጌታ እግዚአብሔርም ከአንተው ጋር ይሁን’ ትላለች።”
2 ሳሙኤል 19:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም እንዲህ አለው፤ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፤ እኔ አገልጋይህ ሽባ በመሆኔ፥ ‘ከንጉሡ ጋር መሄድ እንድችል አህያዬ ይጫንልኝና ልቀመጥበት’ ብዬ ነበር፤ ይሁን እንጂ አገልጋዬ አታለለኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጌታዬ በንጉሡ ፊትም የእኔን የባሪያህን ስም አጥፍቷል፤ መቼም ንጉሥ ጌታዬ እንደ እግዚአብሔር መልአክ ስለ ሆንህ ደስ ያለህን ሁሉ አድርግ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ሆይ! እንዲያውም ስለ እኔ በውሸት ለአንተ የነገረህ ጉዳይ አለ፤ ነገር ግን አንተ እንደ እግዚአብሔር መልአክ ስለ ሆንክ መልካም መስሎ የታየህን አድርግ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም በእኔ በባሪያህ ላይ ክፉ አደረገ፤ አንተ ጌታዬ ንጉሥ ግን እንደ እግዚአብሔር መልአክ ነህ፤ በፊትህም ደስ ያሰኘህን አድርግ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም እኔን ባሪያህን ለጌታዬ ለንጉሡ አማ፥ አንተ ጌታዬ ንጉሥ ግን እንደ እግዚአብሔር መልአክ ነህ፥ ደስም ያሰኘህን አድርግ። |
አሁንም አገልጋይህ፤ ‘ንጉሥ ጌታዬ በጎውንና ክፉውን በመለየት እንደ እግዚአብሔር መልአክ ስለሆነ፥ የጌታዬ የንጉሡ ቃል ያጽናናኝ፤ ጌታ እግዚአብሔርም ከአንተው ጋር ይሁን’ ትላለች።”
አገልጋይህ ኢዮአብ ይህን ያደረገውም የነገሩን መልክ ለመለወጥ ሲል ነው፤ ነገር ግን ጌታዬ ያለው ጥበብ የእግዚአብሔርን መልአክ ጥበብ ስለሚመስል፥ በምድሪቱ ላይ የሚሆነውን ነገር ሁሉ ያውቃል።”
ከዚያም ንጉሡ፥ “የጌታህ ልጅ የት ነው?” ሲል ጠየቀው። ጺባም፥ “ ‘የእስራኤል ቤት ዛሬ የአባቴን መንግሥት ይመልስልኛል’ ብሎ ስለሚያስብ፥ በኢየሩሳሌም ተቀምጦአል” አለው።
ከዚያም ንጉሡ ጺባን፥ “የመፊቦሼት የነበረው ሁሉ ከእንግዲህ ያንተ ነው” አለው። ጺባም፥ “እጅ እነሣለሁ፤ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፤ በፊትህ ሞገስ ላግኝ” አለው።
ንጉሡም፥ “የእግዚአብሔርን ቸርነት እንዳደርግለት ከሳኦል ቤት የቀረ ሰው የለምን?” ሲል ጠየቀው። ጺባም ለንጉሡ፥ “እግሮቹ ሽባ የሆኑ አንድ የዮናታን ልጅ አለ” ብሎ መለሰለት።
አኪሽም እንዲህ አለው፤ “በእኔ ዘንድ እንደ እግዚአብሔር መልአክ መልካም እንደሆንህ ዐውቃለሁ፤ የፍልስጥኤማውያን አዛዦች ግን፥ ‘አብሮን ለጦርነት መውጣት የለበትም’ ብለዋል።