1 ሳሙኤል 29:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 አኪሽም እንዲህ አለው፤ “በእኔ ዘንድ እንደ እግዚአብሔር መልአክ መልካም እንደሆንህ ዐውቃለሁ፤ የፍልስጥኤማውያን አዛዦች ግን፥ ‘አብሮን ለጦርነት መውጣት የለበትም’ ብለዋል። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም9 አንኩስም እንዲህ አለው፤ “በእኔ ዘንድ እንደ እግዚአብሔር መልአክ መልካም እንደ ሆንህ ዐውቃለሁ፤ የፍልስጥኤማውያን አዛዦች ግን፣ ‘ዐብሮን ለጦርነት መውጣት የለበትም’ ብለዋል። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 አኪሽም ዳዊትን መልሶ እንዲህ አለው፦ “አንተ በእኔ አስተያየት እንደ እግዚአብሔር መልአክ ምንም እንከን የሌለብህ መሆኑን ዐውቃለሁ፤ ነገር ግን የፍልስጥኤማውያን ገዢዎች ‘ከእኛ ጋር ወደ ጦርነት መዝመት አይችልም’ አሉ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 አንኩስም መልሶ ዳዊትን፥ “በዐይኔ ፊት ጻድቅ እንደ ሆንህ አውቃለሁ፤ ነገር ግን የፍልስጥኤማውያን አለቆች፦ ‘ከእኛ ጋር ወደ ሰልፍ አይወጣም’ አሉ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 አንኩስም መልሶ ዳዊትን፦ እንደ አምላክ መልእክተኛ በዓይኔ ፊት መልካም እንደ ሆንህ አውቃለሁ፥ ነገር ግን የፍልስጥኤማውያን አለቆች፦ ከእኛ ጋር ወደ ሰልፍ አይወጣም አሉ። ምዕራፉን ተመልከት |