2 ሳሙኤል 19:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም ንጉሡን ለመቀበል ከኢየሩሳሌም በመጣ ጊዜ ንጉሡ፥ “መፊቦሼት፥ አብረኸኝ ያልሄድኸው ለምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም እንዲህ አለው፤ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፤ እኔ አገልጋይህ ሽባ በመሆኔ፣ ‘ከንጉሡ ጋራ መሄድ እንድችል አህያዬ ይጫንልኝና ልቀመጥበት’ ብዬ ነበር፤ ይሁን እንጂ አገልጋዬ ሲባ አታለለኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መፊቦሼትም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ንጉሥ ሆይ፥ እንደምታውቀው እኔ ሽባ ነኝ፤ ከአንተ ጋር ለመሄድ ፈልጌ አገልጋዬን ‘በቅሎዬን ጫንልኝ’ ብለው ከድቶኝ ሄደ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሜምፌቡስቴም አለ፥ “ጌታዬ፥ ንጉሥ፥ አገልጋዬ አታለለኝ፥ እኔ ባሪያህ አንካሳ ነኝና፦ ከንጉሡ ጋር እሄድ ዘንድ አህያዬን ጫንልኝ፤ እኔም እቀመጥበታለሁ አልሁት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም መልሶ አለ፦ ጌታዬ፥ ንጉሥ ሆይ፥ ባሪያዬ አታለለኝ፥ እኔ ባሪያህ አንካሳ ነኝና፦ ከንጉሥ ጋር እሄድ ዘንድ የምቀመጥበትን አህያ ልጫን አልሁት። |
የሳኦል ልጅ ዮናታን ሁለት እግሮቹ ሽባ የሆኑ አንድ ልጅ ነበረው። እርሱም የሳኦልና የዮናታን አሟሟት ወሬ ከኢይዝራኤል በመጣ ጊዜ የአምስት ዓመት ልጅ ነበረ። ሽባ የሆነውንም በዚህ ጊዜ ሞግዚቱ አንሥታው በጥድፊያ ስትሸሽ በመውደቁ ነው። ስሙም መፊቦሼት ይባል ነበር።
ንጉሡም፥ “የእግዚአብሔርን ቸርነት እንዳደርግለት ከሳኦል ቤት የቀረ ሰው የለምን?” ሲል ጠየቀው። ጺባም ለንጉሡ፥ “እግሮቹ ሽባ የሆኑ አንድ የዮናታን ልጅ አለ” ብሎ መለሰለት።