Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 19:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ሜም​ፌ​ቡ​ስ​ቴም አለ፥ “ጌታዬ፥ ንጉሥ፥ አገ​ል​ጋዬ አታ​ለ​ለኝ፥ እኔ ባሪ​ያህ አን​ካሳ ነኝና፦ ከን​ጉሡ ጋር እሄድ ዘንድ አህ​ያ​ዬን ጫን​ልኝ፤ እኔም እቀ​መ​ጥ​በ​ታ​ለሁ አል​ሁት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 እርሱም እንዲህ አለው፤ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፤ እኔ አገልጋይህ ሽባ በመሆኔ፣ ‘ከንጉሡ ጋራ መሄድ እንድችል አህያዬ ይጫንልኝና ልቀመጥበት’ ብዬ ነበር፤ ይሁን እንጂ አገልጋዬ ሲባ አታለለኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 እርሱም ንጉሡን ለመቀበል ከኢየሩሳሌም በመጣ ጊዜ ንጉሡ፥ “መፊቦሼት፥ አብረኸኝ ያልሄድኸው ለምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 መፊቦሼትም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ንጉሥ ሆይ፥ እንደምታውቀው እኔ ሽባ ነኝ፤ ከአንተ ጋር ለመሄድ ፈልጌ አገልጋዬን ‘በቅሎዬን ጫንልኝ’ ብለው ከድቶኝ ሄደ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 እርሱም መልሶ አለ፦ ጌታዬ፥ ንጉሥ ሆይ፥ ባሪያዬ አታለለኝ፥ እኔ ባሪያህ አንካሳ ነኝና፦ ከንጉሥ ጋር እሄድ ዘንድ የምቀመጥበትን አህያ ልጫን አልሁት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 19:26
4 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከእ​ር​ሱም ጋራ ከብ​ን​ያም ወገን የሆኑ ሺህ ሰዎች ነበሩ፤ የሳ​ኦ​ልም ቤት አገ​ል​ጋይ ሲባ ከእ​ር​ሱም ጋር ዐሥራ አም​ስቱ ልጆ​ቹና ሃያው አገ​ል​ጋ​ዮቹ ነበሩ፤ በን​ጉ​ሡም ፊት በቀ​ጥታ ወደ ዮር​ዳ​ኖስ ሄዱ።


ለሳ​ኦ​ልም ልጅ ለዮ​ና​ታን አንድ ሽባ የሆነ ልጅ ነበ​ረው። የሳ​ኦ​ልና የዮ​ና​ታን ወሬ ከኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል በመጣ ጊዜ የአ​ም​ስት ዓመት ልጅ ነበረ፤ ሞግ​ዚ​ቱም አዝ​ላው ሸሸች፤ ልት​ሸ​ሽም ስት​ሮጥ ወድቆ ሽባ ሆነ። ስሙም ሜም​ፌ​ቡ​ስቴ ነበረ።


ንጉ​ሡም፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቸር​ነት አደ​ር​ግ​ለት ዘንድ ከሳ​ኦል ቤት የቀረ ሰው አለን?” አለ። ሲባም ንጉ​ሡን፥ “እግ​ሮቹ ሽባ የሆኑ አንድ የዮ​ና​ታን ልጅ አለ” አለው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች