2 ሳሙኤል 19:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)25 የሳኦል ልጅ መፊቦሼትም ንጉሡን ለመቀበል ወረደ። ንጉሡ ከተሰደደበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ተመለሰበት ዕለት ድረስ ለእግሩ መጫሚያ አላደረገም፤ ጢሙን አልተላጨም፤ ልብሱንም አላጠበም ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም25 እርሱም ንጉሡን ለመቀበል ከኢየሩሳሌም በመጣ ጊዜ ንጉሡ፣ “ሜምፊቦስቴ፣ ዐብረኸኝ ያልሄድኸው ለምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም25 መፊቦሼት ከኢየሩሳሌም ተነሥቶ ንጉሡን በሚቀበልበት ስፍራ በደረሰ ጊዜ ንጉሡ “መፊቦሼት ሆይ፥ ስለምን ከእኔ ጋር ሳትሄድ ቀረህ?” አለው። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)25 ከዚህም በኋላ ንጉሡን ሊቀበለው ከኢየሩሳሌም በመጣ ጊዜ ንጉሡ፥ “ሜምፌቡስቴ፥ ከእኔ ጋር ስለምን አልወጣህም?” አለው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)25 ንጉሡም ሊቀበለው ከኢየሩሳሌም በመጣ ጊዜ ንጉሡ፦ ሜምፊቦስቴ ሆይ፥ ከእኔ ጋር ስለ ምን አልወጣህም? አለው። ምዕራፉን ተመልከት |