2 ሳሙኤል 18:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሒማዓጽም ጮኾ ንጉሡን፥ “ሁሉም ደህና ሆኖአል” አለ፤ ከዚያም ወደ መሬት ለጥ ብሎ በንጉሡ ፊት እጅ ነሣና፥ “በጌታዬ በንጉሡ ላይ እጃቸውን ያነሡትን ሰዎች አሳልፎ የሰጠ ጌታ አምላክህ የተመሰገነ ይሁን!” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አኪማአስም ጮኾ ንጉሡን፣ “ሁሉም ነገር ተሳክቷል” አለ፤ ከዚያም ወደ መሬት ለጥ ብሎ በንጉሡ ፊት እጅ ነሣና፣ “በጌታዬ በንጉሡ ላይ እጃቸውን ያነሡትን ሰዎች አሳልፎ የሰጠ አምላክ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን!” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሒማዓጽም ድምፁን ከፍ አድርጎ ለንጉሡ ሰላምታ ሰጠ፤ በንጉሡም ፊት በግንባሩ መሬት ላይ ተደፍቶ “ንጉሥ ሆይ! በአንተ ላይ በዐመፅ የተነሣሡትን ድል እንድታደርግ ስለ ረዳህ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን!” አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አኪማሖስም ጮኾ ንጉሡን፥ “ሰላም ለአንተ ይሁን!” አለው። በንጉሡም ፊት በምድር ላይ በግንባሩ ሰግዶ፥ “በንጉሡ በጌታዬ ላይ እጃቸውን ያነሡትን ሰዎች አሳልፎ የሰጠ አምላክህ እግዚአብሔር ይመስገን” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አኪማአስም ጮኾ ንጉሡን፦ ሁሉ ደህና ሆኖአል አለው። በንጉሡም ፊት በምድር ላይ በግንባሩ ተደፍቶ፦ በንጉሡ በጌታዬ ላይ እጃቸውን ያነሡትን ሰዎች አሳልፎ የሰጠ አምላክህ እግዚአብሔር ይመስገን አለ። |
እንዲህም አለ፦ “ቸርነቱንና እውነቱን ከጌታዬ ያላራቀ የጌታዬ የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን፥ እኔ በመንገድ ሳለሁ እግዚአብሔር ወደ ጌታዬ ወንድሞች ቤት መራኝ።”
በሦስተኛውም ቀን፥ እነሆ፥ የተቀደደ ልብስ የለበሰ፥ በራሱም ላይ ትቢያ የነሰነሰ አንድ ሰው ከሳኦል ሰፈር መጣ። ወደ ዳዊት መጥቶም በግምባሩ በመደፋት እጅ ነሣ።
ጌታ ዛሬ አንተን በእጄ አሳልፎ ይሰጣል፤ እኔ መትቼ እጥልሃለሁ፤ ራስህንም እቆርጠዋለሁ። በዚህች ዕለት የፍልስጥኤማውያንን ሠራዊት ሬሣ ለሰማይ አሞሮችና ለምድር አራዊት እሰጣለሁ፤ ዓለምም ሁሉ በእስራኤል ዘንድ እግዚአብሔር መኖሩን ያውቃል።
አቢሳም ዳዊትን፥ “ዛሬ እግዚአብሔር ጠላትህን በእጅህ ላይ ጥሎታል፤ አሁንም እኔ አንድ ጊዜ በጦር ወግቼ ከመሬት ጋር ላጣብቀው፤ መድገምም አያስፈልገኝም” አለው።