Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 14:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ልዑል እግዚአብሔርም ይባረክ፤ ጠላቶችህን በእጅህ የጣለልህ። አብራምም ከሁሉ አሥራትን ሰጠው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ጠላቶችህን አሳልፎ በእጅህ የሰጠህ፣ ልዑል አምላክ ይባረክ።” አብራምም ከሁሉ ነገር ዐሥራትን አውጥቶ ሰጠው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 በጠላቶችህ ላይ ድልን ያቀዳጀህ፥ ልዑል እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን።” አብራምም በምርኮ ካገኘው ሀብት ሁሉ አንድ ዐሥረኛውን ለመልከ ጼዴቅ ሰጠው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ጠላ​ቶ​ች​ህን በእ​ጅህ የጣ​ለ​ልህ ልዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቡሩክ ነው” አለው። አብ​ራ​ምም ከሁሉ ዐሥ​ራ​ትን ሰጠው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ጠላቶችህን በእጅህ የጣለልህ ልዑል እግዚአብሔርም የተባረከ ነው አለውም። አብራምም ከሁሉ አሥራትን ሰጠው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 14:20
30 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የሰዶም ንጉሥም አብራምን፦ ሰዎቹን ስጠኝ፥ ከብቱን ግን ለአንተ ውሰድ አለው።


እንዲህም አለ፦ “ቸርነቱንና እውነቱን ከጌታዬ ያላራቀ የጌታዬ የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን፥ እኔ በመንገድ ሳለሁ እግዚአብሔር ወደ ጌታዬ ወንድሞች ቤት መራኝ።”


ለሐውልት የተከልሁት ይህም ድንጋይ የእግዚአብሔር ቤት ይሆናል፥ ከሰጠኸኝም ሁሉ ለአንተ ከዐሥር እጅ አንዱን እሰጥሃለሁ።”


በመከርም ጊዜ ፍሬውን ከአምስት እጅ አንዱን እጅ ለፈርዖን ስጡ፥ አራቱም እጅ ለእናንተ ለራሳችሁ፥ ለእርሻው ዘርና ለእናንተ ምግብ፥ ለቤተ ሰዋችሁና ለሕፃናቶቻችሁም ምግብ ይሁን።”


ዮሴፍም ለፈርዖን ካልሆነችው ከካህናቱ ምድር በቀር አምስተኛው እጅ ለፈርዓን እንዲሆን በግብጽ ምድር እስከ ዛሬ ድረስ ሕግ አደረጋት።


ደግሞም እንዲህ አለ፦ “የሴም ጌታ እግዚእብሔር ይባረክ! ከነዓንም የሴም አገልጋይ ይሁን!


አሒማዓጽም ጮኾ ንጉሡን፥ “ሁሉም ደህና ሆኖአል” አለ፤ ከዚያም ወደ መሬት ለጥ ብሎ በንጉሡ ፊት እጅ ነሣና፥ “በጌታዬ በንጉሡ ላይ እጃቸውን ያነሡትን ሰዎች አሳልፎ የሰጠ ጌታ አምላክህ የተመሰገነ ይሁን!” አለ።


ቁርባኑና አሥራቱን የተቀደሱትንም ነገሮች በታማኝነት ወደዚያ አስገቡ። ሌዋዊውም ኮናንያ ተሾመባቸው፥ ወንድሙም ሰሜኢ በማዕረግ ሁለተኛ ነበረ፤


የእህላችንንም በኵራት፥ የእጅ ማንሣታችንን ቁርባን፥ የዛፍ ሁሉ ፍሬ፥ ወይኑንና ዘይቱንም ወደ ካህናቱ ወደ አምላካችን ቤት ጓዳዎች እናመጣ ዘንድ፥ ሌዋውያኑም ከከተሞቻችን እርሻ ሁሉ አሥራት ይቀበላሉና የመሬታችንን አሥራት ወደ ሌዋውያን እናመጣ ዘንድ ማልን።


ይሁዳም ሁሉ የእህሉንና የወይኑን የዘይቱንም አሥራት ወደ ዕቃ ቤቶች አመጡ።


ስለ ጎልያድ፥ የዳዊት መዝሙር። ጌታዬ ዐለቴ፥ ይባረክ፥ ለእጆቼ ሰልፍን፥ ለጣቶቼም ዘመቻን የሚያስተምር፥


እጅህ አሕዛብን አባረረች፥ እነርሱንም ተከልህ፥ አሕዛብን አስጨንቀህ እነሱን አለመለምክ።


ወደ ላይ ዓረግህ፥ ምርኮን ማረክህ፥ ስጦታንም ከሰዎች ወሰድህ፥ ከዓመፀኞችም ጭምር፥ በዚያም ጌታ ያድር ዘንድ።


ይትሮም እንዲህ አለ፦ “ከግብጽ እጅና ከፈርዖን እጅ ያዳናችሁ፥ ከግብጽም እጅ በታች ሕዝቡን ያዳነ ጌታ ይባረክ።


“የእስራኤል ልጆች ሆይ! ይህን ወድዳችኋልና ወደ ቤቴል ኑና ኃጢአትን ሥሩ፤ ወደ ጌልገላ ኑና ኃጢአትን አብዙ፤ በየማለዳውም መሥዋዕታችሁን፥ በየሦስተኛውም ቀን አሥራታችሁን አምጡ፤


በቤቴ ውስጥ መብል እንዲሆን አሥራቱን ሁሉ ወደ ጎተራ አስገቡ፤ የሰማያቶችን መስኮቶች ባልከፍትላችሁ፥ በረከትንም አትረፍርፌ ባላፈስስላችሁ በዚህ ፈትኑኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ።


ሰው እግዚአብሔርን ይሰርቃልን? እናንተ ግን ሰርቃችሁኛል። እናንተም፦ እንዴት እንሰርቅሃለን? ብላችኋል። በአሥራትና በቁርባን ነው።


“ደግሞ በበኵራት ቀን ከሰባቱ ሱባዔ በዓላችሁ አዲሱን የእህል ቁርባን ለጌታ ባቀረባችሁ ጊዜ፥ የተቀደሰ ጉባኤ ይኑራችሁ፤ የጉልበት ሥራ ሁሉ አትሥሩበት።


በየሳምንቱ ሁለት ጊዜ እጾማለሁ፤ ከማገኘውም ሁሉ አሥራት እሰጣለሁ፤’ አለ።


በእግዚአብሔር ወንጌል እንደ ካህን እያገለገልሁ፥ ለአሕዛብ የክርስቶስ ኢየሱስ አገልጋይ እንድሆን ነው፥ ይህም አሕዛብ በመንፈስ ቅዱስ ተቀድሰው የተወደደ መሥዋዕት እንዲሆኑ ነው።


በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ በሰማያዊ ስፍራ በክርስቶስ የባረከን፥ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይባረክ።


የእህልህን፥ የወይን ጠጅህንና የዘይትህን አሥራት፥ ወይም የቀንድ ከብት፥ የበግና የፍየል መንጋህን በኵራት፥ ወይም ለመስጠት የተሳልኸውን ወይም የፈቃድህን ስጦታ፥ ወይም የእጅህን ስጦታ፥ በከተሞችህ ውስጥ መብላት የለብህም።


ምንጊዜም ጌታ እግዚአብሔርን ማክበር ትማር ዘንድ፥ የወይን ጠጅና የዘይትህን አሥራት፥ የቀንድ ከብትህን፥ የበግና የፍየል መንጋህን በኵራት ስሙ እንዲጠራበት በሚመርጠው ስፍራ፥ በጌታ በእግዚአብሔር ፊት ትበላለህ።


“በየሦስት ዓመቱም መጨረሻ የዚያን ዓመት ሰብል አሥራት በሙሉ አውጥተህ በከተሞችህ ውስጥ አከማች።


የእስራኤልም አምላክ ጌታ ለእስራኤል ስለ ተዋጋላቸው ኢያሱ እነዚህን ነገሥታት ሁሉ ምድራቸውንም በአንድ ጊዜ ያዘ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች