ከዚያም ጠባቂው ሌላ ሰው ሲሮጥ አየ፤ ዘበኛውን ተጣራና፥ “ተመልከት! ሌላም ሰው ብቻውን እየሮጠ በመምጣት ላይ ነው!” አለው። ንጉሡም፥ “ይኸኛውም መልካም ወሬ ይዞ የመጣ ይሆናል” አለ።
2 ሳሙኤል 18:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጠባቂውም፥ “የመጀመሪያው ሰው ሩጫ የሳዶቅን ልጅ የአሒማዓጽን ሩጫ ይመስለኛል” አለ። ንጉሡም፥ “እርሱ ጥሩ ሰው ነው፤ ቢመጣም የምሥራች ይዞ ነው” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጠባቂውም፣ “የመጀመሪያው ሰው ሩጫ የሳዶቅን ልጅ የአኪማአስን ሩጫ ይመስለኛል” አለ። ንጉሡም፣ “እርሱማ ጥሩ ሰው ነው፤ የምሥራች ሳይዝ አይመጣም” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዘበኛውም “የመጀመሪያው ሰው የሚሮጠው ልክ እንደ ሳዶቅ ልጅ አሒማዓጽ ነው” አለ። ንጉሡም “እርሱ ጥሩ ሰው ነው፤ መልካም ወሬ ይዞ ይመጣል” አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዘበኛውም፥ “የፊተኛው ሩጫ እንደ ሳዶቅ ልጅ እንደ አኪማሖስ ሩጫ ይመስላል” አለ፤ “ንጉሡም፦ እርሱ መልካም ሰው ነው፤ መልካምም ወሬ ያመጣል” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዘበኛውም፦ የፊተኛው ሩጫ እንደ ሳዶቅ ልጅ እንደ አኪማአስ ሩጫ ይመስላል አለ፥ ንጉሡም እርሱ መልካም ሰው ነው፥ መልካም ወሬ ያመጣል አለ። |
ከዚያም ጠባቂው ሌላ ሰው ሲሮጥ አየ፤ ዘበኛውን ተጣራና፥ “ተመልከት! ሌላም ሰው ብቻውን እየሮጠ በመምጣት ላይ ነው!” አለው። ንጉሡም፥ “ይኸኛውም መልካም ወሬ ይዞ የመጣ ይሆናል” አለ።
“ዘበኛውም እንደገና መልእክተኛው በመምጣት ላይ ወዳለው ጭፍራ ደርሶአል፤ ነገር ግን ተመልሶ አልመጣም” ካለ በኋላ “የጭፍራው መሪ ሠረገላ አነዳዱ እንደ እብድ ሰው ነው! እንዲያውም ልክ ኢዩን ይመስላል!” ሲል ተናገረ።
የምሥራች የሚናገር፥ ሰላምንም የሚያወራ፥ የመልካምንም ወሬ የምሥራች የሚናገር፥ መድኃኒትንም የሚያወራ፥ ጽዮንንም፦ አምላክሽ ነግሦአል የሚል ሰው እግሩ በተራሮች ላይ እጅግ ውብ ነው።