2 ሳሙኤል 18:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢዮአብም፥ “ከእንግዲህ በዚህ ሁኔታ ከአንተ ጋር ጊዜ ማጥፋት አልችልም” አለው፤ ስለዚህ በእጁ ሦስት ጦር ይዞ ሄደና አቤሴሎም እባሉጥ ዛፉ ላይ ተንጠልጥሎ ገና በሕይወት እያለ ወርውሮ በልቡ ላይ ተከላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢዮአብም፣ “ከእንግዲህ በዚህ ሁኔታ ከአንተ ጋራ ጊዜ ማጥፋት አልችልም” አለው፤ ስለዚህ በእጁ ሦስት ጦር ይዞ ሄደና አቤሴሎም እዛፉ ላይ ተንጠልጥሎ ገና በሕይወት እያለ፣ ወርውሮ በልቡ ላይ ተከላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዮአብም “እኔ አሁን ከአንተ ጋር ጊዜ ማባከን አልፈልግም” አለውና ሦስት ጦሮችን ወስዶ አቤሴሎም በወርካው ዛፍ ላይ ተንጠልጥሎ ገና በሕይወት ሳለ በደረቱ ተከለበት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዮአብም፥ “እኔ ከአንተ ጋር እንዲህ እዘገይ ዘንድ አልችልም” ብሎ ሦስት ጦሮች በእጁ ወሰደ፤ አቤሴሎምም ገና በዛፍ ላይ ተንጠልጥሎ ሕያው ሳለ በልቡ ላይ ተከላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዮአብም፦ እኔ ከአንተ ጋር እንዲህ እዘገይ ዘንድ አልችልም ብሎ ሦስት ጦሮች በእጁ ወሰደ፥ አቤሴሎምም ገና በዛፍ ላይ ተንጠልጥሎ ሕያው ሳለ በልቡ ላይ ተከላቸው። |
ከዚያም አቤሴሎም ለአገልጋዮቹ “ተመልከቱ፥ የኢዮአብ እርሻ የሚገኘው ከእኔ እርሻ አጠገብ ነው፤ በእርሻው ላይ የገብስ ሰብል አለው፤ ሄዳችሁም እሳት ልቀቁበት” አላቸው። ስለዚህ የአቤሴሎም አገልጋዮች ሄደው እርሻውን በእሳት አቃጠሉት።
ንጉሡም ኢዮአብን፥ አቢሳንና ኢታይን፥ “ለእኔ ስትሉ በወጣቱ ልጄ በኤቤሴሎም ላይ ጉዳት እንዳታደርሱበት” ብሎ አዘዛቸው። ንጉሡ ልጁን አቤሴሎምን አስመልክቶ ለአዛዥዎቹ ትእዛዝ ሲሰጥ ሕዝቡ ሁሉ ሰማ።
ንጉሡም እጅግ አዘነ፤ በቅጽር በሩ ዐናት ላይ ወዳለችው ቤት ወጥቶ አለቀሰ፤ ሲሄድም፥ “ልጄ አቤሴሎም ሆይ! ልጄ አቤሴሎም! በአንተ ፈንታ ምነው እኔ በሞትሁ ኖሮ! አቤሴሎም፥ ልጄን፥ ወየው ልጄን!” ይል ነበር።
ዮናስ በዓሣ ነባሪ ሆድ ውስጥ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ፥ እንዲሁም የሰው ልጅ በምድር ልብ ውስጥ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይቆያል።
እነርሱም፦ “ሰላምና ደኅንነት ነው” በሚሉ ጊዜ ምጥ እንደ ያዛት እርጉዝ ሴት ድንገተኛ ጥፋት በእነርሱ ላይ ይመጣባቸዋል፤ ከቶም አያመልጡም።
የሔቤር ሚስት ያዔል ግን ሲሣራ ደክሞ፥ ከባድ እንቅልፍም ወስዶት ሳለ፥ የድንኳን ካስማና መዶሻ ይዛ በቀስታ ወደ እርሱ ቀረበች፤ ከዚያም ካስማውን በመዶሻ ጆሮ ግንዱ ላይ መትታ ከመሬት ጋር ሰፋችው፤ እርሱም ሞተ።
እጅዋን ወደ ካስማ፥ ቀኝ እጅዋንም ወደ ሠራተኛ መዶሻ አደረገች፥ በመዶሻውም ሲሣራን መታች፥ ራሱንም ቸነከረች፥ ጆሮግንዱንም በሳች፥ ጎዳችውም።
አቤቱ፥ ጠላቶችህ ሁሉ እንዲሁ ይጥፉ፥ ወዳጆችህ ግን ፀሐይ በኃይሉ በወጣ ጊዜ እንደሚሆን፥ እንዲሁ ይሁኑ። ምድሪቱም አርባ ዓመት ያህል ዐረፈች።