35 ክፉን በጭቆና ከፍ ከፍ ብሎ እንደ ሊባኖስ ዝግባም ለምልሞ አየሁት።
35 ክፉና ጨካኙን ሰው፣ እንደ ሊባኖስ ዝግባ ለምልሞ አየሁት፤
35 አንድ ጨካኝና ክፉ ሰው በሀገሩ መሬት እንደ ለመለመ ዛፍ ተጠናክሮ አየሁ።
ኢዮአብም፥ “ከእንግዲህ በዚህ ሁኔታ ከአንተ ጋር ጊዜ ማጥፋት አልችልም” አለው፤ ስለዚህ በእጁ ሦስት ጦር ይዞ ሄደና አቤሴሎም እባሉጥ ዛፉ ላይ ተንጠልጥሎ ገና በሕይወት እያለ ወርውሮ በልቡ ላይ ተከላቸው።
እንዲሁም ከኢዮአብ ጋሻ ጃግሬዎች ዐሥሩ አቤሴሎምን በመክበብ ወግተው ገደሉት።
አላዋቂውን ሰው ሥር ሰድዶ አየሁት፥ ድንገትም መኖሪያውን ረገምሁ።
ተክለሃቸዋል፤ ሥርም ሰድደዋል፤ አድገዋል ፍሬም አፍርተዋል፤ በአፋቸው አንተ ቅርብ ነህ፥ ከልባቸው ግን ሩቅ ነህ።
በክብርና በታላቅነት ከዔድን ዛፎች መካከል እንግዲህ ማንን ትመስላለህ? ሆኖም ከዔድን ዛፎች ጋር ወደ ታችኛው ምድር ትወርዳለህ፥ በሰይፍ በተገደሉት ባልተገረዙት መካከል ትጋደማለህ። ይህም ፈርዖንና ብዛቱ ሁሉ ነው፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ስለዚህ ቁመቱ ከሜዳ ዛፍ ሁሉ በላይ በለጠ፥ ቅርንጫፎቹም በዙ፥ በለቀቀላቸውም ጊዜ ከብዙ ውኆች የተነሣ ቅርንጫፎቹ ረዘሙ።