ነገር ግን ወደ ከተማዪቱ ተመልሰህ አቤሴሎምን፥ ‘ንጉሥ ሆይ፤ አገልጋይህ እሆናለሁ፤ ቀድሞ የአባትህ አገልጋይ እንደ ነበርሁ ሁሉ፥ ዛሬም አንተን አገለግልሃለሁ’ ብትለው የአኪጦፌልን ምክር በማፍረስ ትረዳኛለህ።
2 ሳሙኤል 16:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ ልጁን ካላገለገልሁ ማንን ላገለግል ነው? አባትህን እንዳገለገልሁ ሁሉ፤ አንተንም አገለግላለሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ ልጁን ካላገለገልሁ ማንን ላገለግል ነው? አባትህን እንዳገለገልሁ ሁሉ፤ አንተንም አገለግላለሁ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለመሆኑ የጌታዬን ልጅ ካላገለገልኩ ማንን ላገለግል ነው? ስለዚህ አባትህን እንዳገለገልኩ አሁንም ደግሞ አንተን አገለግላለሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ዳግምም የማገለግል ለማን ነው? በንጉሥ ልጅ ፊት አይደለምን? በአባትህ ፊት እንዳገለገልሁ እንዲሁ በአንተ ፊት እሆናለሁ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳግምም የማገለግል ለማን ነው? በንጉሥ ልጅ ፊት አይደለምን? በአባትህ ፊት እንዳገለገልሁ እንዲሁ በአንተ ፊት እሆናለሁ አለው። |
ነገር ግን ወደ ከተማዪቱ ተመልሰህ አቤሴሎምን፥ ‘ንጉሥ ሆይ፤ አገልጋይህ እሆናለሁ፤ ቀድሞ የአባትህ አገልጋይ እንደ ነበርሁ ሁሉ፥ ዛሬም አንተን አገለግልሃለሁ’ ብትለው የአኪጦፌልን ምክር በማፍረስ ትረዳኛለህ።
ሑሻይም፥ አቤሴሎምን እንዲህ አለው፤ “እንዲህስ አይሆንም! እኔ በጌታ፥ በዚህ ሕዝብና በእስራኤል ሰዎች ሁሉ ለተመረጠው ለእርሱ እሆናለሁ፤ አብሬውም እኖራለሁ፤
ዳዊትም፥ “አገልጋይህ ምን እንደሚያደርግ ያንጊዜ አንተው ራስህ ታያለህ” አለው። አኪሽም፥ “መልካም፤ በዘመኔ ሁሉ የራሴ የክብር ዘብ አደርግሃለሁ” ሲል መለሰለት።
ዳዊትም ለአኪሽ፥ “ለመሆኑ ምን አደረግሁ? እዚህ ከመጣሁበት ዕለት ጀምሮ እስካሁን ድረስ፥ በአገልጋይህ ላይ ምን አገኘህበት? ታዲያ፥ ከንጉሡ ከጌታዬ ጠላቶች ጋር የማልዋጋው ስለ ምንድነው?” ብሎ ጠየቀው።