Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 16:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ለመሆኑ የጌታዬን ልጅ ካላገለገልኩ ማንን ላገለግል ነው? ስለዚህ አባትህን እንዳገለገልኩ አሁንም ደግሞ አንተን አገለግላለሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 እንግዲህ ልጁን ካላገለገልሁ ማንን ላገለግል ነው? አባትህን እንዳገለገልሁ ሁሉ፤ አንተንም አገለግላለሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 እንግዲህ ልጁን ካላገለገልሁ ማንን ላገለግል ነው? አባትህን እንዳገለገልሁ ሁሉ፤ አንተንም አገለግላለሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 “ዳግ​ምም የማ​ገ​ለ​ግል ለማን ነው? በን​ጉሥ ልጅ ፊት አይ​ደ​ለ​ምን? በአ​ባ​ትህ ፊት እን​ዳ​ገ​ለ​ገ​ልሁ እን​ዲሁ በአ​ንተ ፊት እሆ​ና​ለሁ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ዳግምም የማገለግል ለማን ነው? በንጉሥ ልጅ ፊት አይደለምን? በአባትህ ፊት እንዳገለገልሁ እንዲሁ በአንተ ፊት እሆናለሁ አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 16:19
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አንተ እኔን ልትረዳኝ የምትችለው ግን ወደ ከተማይቱ ተመልሰህ አቤሴሎምን፥ አባትህን እንዳገለገልኩ አንተንም በታማኝነት አገለግላለሁ ብለህ ብትነግረው እንዲሁም አኪጦፌል የሚሰጠውን ምክር ሁሉ ብትቃወምልኝ ነው፤


ንግግሩ እንደ ቅቤ የለዘበ ነው፤ በልቡ የሚያስበው ግን ጦርነትን ነበር አንደበቱ ከዘይት ይበልጥ የለሰለሰ ነው፤ ነገር ግን እንደ ተመዘዘ ሰይፍ ነው።


አንዳንድ ከአይሁድ ወገን የሆኑ ክርስቲያኖችም የጴጥሮስን ግብዝነት ተከተሉ፤ በርናባስ እንኳ ሳይቀር በግብዝነታቸው ተስቦ ነበር።


ዳዊትም “ጌታዬ ምን በደል ሠራሁ? አንተን ማገልገል ከጀመርኩበት ጊዜ አንሥቶ በደል ካልተገኘብኝ ጌታዬና ንጉሤ የሆንከውን አንተን ተከትዬ በመዝመት ጠላቶችህን መውጋት የማልችለው ስለምንድን ነው?” አለው።


ዳዊትም “እኔ አገልጋይህ ነኝ፤ የማደርገውንም አንተ ራስህ ማየት ትችላለህ” ሲል መለሰለት። አኪሽም “መልካም ነው! እኔ አንተን ለዘለቄታ የራሴ የክብር ዘብ አደርግሃለሁ!” አለው።


ሑሻይም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “እንዴት እኔ ይህንን አደርጋለሁ? እኔ ምንጊዜም በዚህ ሕዝብና በመላው እስራኤል እንዲሁም በእግዚአብሔር የተመረጠው ሰው ወገን ነኝ፤ አሁንም ከአንተ ጋር እኖራለሁ፤


ከዚህ በኋላ አቤሴሎም ወደ አኪጦፌል መለስ ብሎ “እነሆ እኛ አሁን በዚህ ተገኝተናል፤ ታዲያ ምን እንድናደርግ ትመክረናለህ?” ሲል ጠየቀው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች