2 ሳሙኤል 16:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሑሻይም፥ አቤሴሎምን እንዲህ አለው፤ “እንዲህስ አይሆንም! እኔ በጌታ፥ በዚህ ሕዝብና በእስራኤል ሰዎች ሁሉ ለተመረጠው ለእርሱ እሆናለሁ፤ አብሬውም እኖራለሁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኩሲም፣ አቤሴሎምን እንዲህ አለው፤ “ይህንስ አላዳርገውም! እኔ በእግዚአብሔር፣ በዚህ ሕዝብና በእስራኤል ሰዎች ሁሉ ለተመረጠው ለርሱ እሆናለሁ፤ አብሬውም እኖራለሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሑሻይም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “እንዴት እኔ ይህንን አደርጋለሁ? እኔ ምንጊዜም በዚህ ሕዝብና በመላው እስራኤል እንዲሁም በእግዚአብሔር የተመረጠው ሰው ወገን ነኝ፤ አሁንም ከአንተ ጋር እኖራለሁ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኩሲም አቤሴሎምን፥ “እንዲህ አይደለም፤ እግዚአብሔር፥ ይህም ሕዝብ፥ የእስራኤልም ሰዎች ሁሉ ለመረጡት ለእርሱ እሆናለሁ፤ ከእርሱም ጋር እኖራለሁ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኩሲም አቤሴሎምን፦ እንዲህ አይደለም፥ ከእግዚአብሔር ከዚህም ሕዝብ ከእስራኤልም ሰዎች ሁሉ ለተመረጠው ለእርሱ እሆናለሁ ከእርሱም ጋር እቀመጣለሁ። |
ሳሙኤልም የዘይቱን ቀንድ ወስዶ በወንድሞቹ ፊት ቀባው። ከዚያ ቀን ጀምሮ የጌታ መንፈስ በዳዊት ላይ በኃይል መጣ፤ ሳሙኤልም ወደ ራማ ተመለሰ።