Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 16:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ኩሲም አቤ​ሴ​ሎ​ምን፥ “እን​ዲህ አይ​ደ​ለም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ ይህም ሕዝብ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ሁሉ ለመ​ረ​ጡት ለእ​ርሱ እሆ​ና​ለሁ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር እኖ​ራ​ለሁ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ኩሲም፣ አቤሴሎምን እንዲህ አለው፤ “ይህንስ አላዳርገውም! እኔ በእግዚአብሔር፣ በዚህ ሕዝብና በእስራኤል ሰዎች ሁሉ ለተመረጠው ለርሱ እሆናለሁ፤ አብሬውም እኖራለሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ሑሻይም፥ አቤሴሎምን እንዲህ አለው፤ “እንዲህስ አይሆንም! እኔ በጌታ፥ በዚህ ሕዝብና በእስራኤል ሰዎች ሁሉ ለተመረጠው ለእርሱ እሆናለሁ፤ አብሬውም እኖራለሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ሑሻይም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “እንዴት እኔ ይህንን አደርጋለሁ? እኔ ምንጊዜም በዚህ ሕዝብና በመላው እስራኤል እንዲሁም በእግዚአብሔር የተመረጠው ሰው ወገን ነኝ፤ አሁንም ከአንተ ጋር እኖራለሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ኩሲም አቤሴሎምን፦ እንዲህ አይደለም፥ ከእግዚአብሔር ከዚህም ሕዝብ ከእስራኤልም ሰዎች ሁሉ ለተመረጠው ለእርሱ እሆናለሁ ከእርሱም ጋር እቀመጣለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 16:18
4 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሳሙ​ኤ​ልም የዘ​ይ​ቱን ቀንድ ወስዶ በወ​ን​ድ​ሞቹ መካ​ከል ቀባው። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ ከዚያ ቀን ጀምሮ በዳ​ዊት ላይ መጣ። ሳሙ​ኤ​ልም ተነ​ሥቶ ወደ አር​ማ​ቴም ሄደ።


አቤ​ሴ​ሎ​ምም ኩሲን፥ “ስለ ወዳ​ጅህ ያደ​ረ​ግ​ኸው ቸር​ነት ይህ ነውን? ከወ​ዳ​ጅህ ጋር ያል​ሄ​ድህ ስለ ምን​ድን ነው?” አለው።


“ዳግ​ምም የማ​ገ​ለ​ግል ለማን ነው? በን​ጉሥ ልጅ ፊት አይ​ደ​ለ​ምን? በአ​ባ​ትህ ፊት እን​ዳ​ገ​ለ​ገ​ልሁ እን​ዲሁ በአ​ንተ ፊት እሆ​ና​ለሁ” አለው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች