Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 16:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ሑሻይም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “እንዴት እኔ ይህንን አደርጋለሁ? እኔ ምንጊዜም በዚህ ሕዝብና በመላው እስራኤል እንዲሁም በእግዚአብሔር የተመረጠው ሰው ወገን ነኝ፤ አሁንም ከአንተ ጋር እኖራለሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ኩሲም፣ አቤሴሎምን እንዲህ አለው፤ “ይህንስ አላዳርገውም! እኔ በእግዚአብሔር፣ በዚህ ሕዝብና በእስራኤል ሰዎች ሁሉ ለተመረጠው ለርሱ እሆናለሁ፤ አብሬውም እኖራለሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ሑሻይም፥ አቤሴሎምን እንዲህ አለው፤ “እንዲህስ አይሆንም! እኔ በጌታ፥ በዚህ ሕዝብና በእስራኤል ሰዎች ሁሉ ለተመረጠው ለእርሱ እሆናለሁ፤ አብሬውም እኖራለሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ኩሲም አቤ​ሴ​ሎ​ምን፥ “እን​ዲህ አይ​ደ​ለም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ ይህም ሕዝብ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ሁሉ ለመ​ረ​ጡት ለእ​ርሱ እሆ​ና​ለሁ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር እኖ​ራ​ለሁ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ኩሲም አቤሴሎምን፦ እንዲህ አይደለም፥ ከእግዚአብሔር ከዚህም ሕዝብ ከእስራኤልም ሰዎች ሁሉ ለተመረጠው ለእርሱ እሆናለሁ ከእርሱም ጋር እቀመጣለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 16:18
4 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አቤሴሎምም “ለወዳጅህ ለዳዊት የነበረህ ታማኝነት እንደዚህ ነበርን? እርሱንስ ተከትለህ ለምን አልሄድክም?” ሲል ጠየቀው።


ለመሆኑ የጌታዬን ልጅ ካላገለገልኩ ማንን ላገለግል ነው? ስለዚህ አባትህን እንዳገለገልኩ አሁንም ደግሞ አንተን አገለግላለሁ።”


ሳሙኤልም በወይራ ዘይት የተሞላውን ቀንድ ወስዶ ዳዊትን በወንድሞቹ ፊት ቀባው፤ ወዲያውኑ የእግዚአብሔር መንፈስ በዳዊት አደረበት፤ ከዚያም ቀን ጀምሮ ከእርሱ አልተለየም፤ ከዚህም በኋላ ሳሙኤል ወደ ራማ ተመለሰ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች