2 ሳሙኤል 15:37 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ የዳዊት ወዳጅ ሑሻይ ልክ አቤሴሎም ኢየሩሳሌም በገባበት ሰዓት ወደ ከተማዋ ደረሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ የዳዊት ወዳጅ ኩሲ ልክ አቤሴሎም ኢየሩሳሌም በገባበት ሰዓት እዚያው ከተማ ደረሰ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም የዳዊት ወዳጅ ሑሻይ ወደ ከተማይቱ ተመለሰ፤ አቤሴሎምም ወዲያውኑ እዚያ ደረሰ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዳዊትም ወዳጅ ኩሲ ወደ ከተማ መጣ፤ አቤሴሎምም ደግሞ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዳዊትም ወዳጅ ኩሲ ወደ ከተማ መጣ፥ አቤሴሎምም ደግሞ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ። |