Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ነገሥት 4:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ዓዛርያስ የተባለው የናታን ልጅ፦ የክፍላተ ሀገር ገዢዎች የበላይ ኀላፊ፤ የናታን ልጅ ካህኑ ዛቡድ፦ የንጉሡ አማካሪና ወዳጅ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 የናታን ልጅ ዓዛርያስ፣ የአውራጃ ገዦች የበላይ ኀላፊ፤ የናታን ልጅ ዛቡድ፣ ካህንና የንጉሡ የቅርብ አማካሪ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ዓዛርያስ የተባለው የናታን ልጅ፦ የክፍላተ ሀገር ገዢዎች የበላይ ኀላፊ፤ የናታን ልጅ ካህኑ ዛቡድ፦ የንጉሡ አማካሪና ወዳጅ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 የና​ታ​ንም ልጅ ኦርኒያ የሹ​ሞች አለቃ ነበረ፤ የና​ታ​ንም ልጅ ዘባት የን​ጉሡ አማ​ካ​ሪና ወዳጅ ነበረ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 የናታንም ልጅ ዓዛርያስ የሹሞች አለቃ ነበረ፤ የናታንም ልጅ ዛቡድ የንጉሡ አማካሪና ወዳጅ ነበረ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ነገሥት 4:5
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አኪጦፌልም የንጉሡ አማካሪ ነበረ፤ አርካዊውም ኩሲ የንጉሡ ወዳጅ ነበረ፤


የዳዊት ወዳጅ አርካዊው ሑሻይም ወደ አቤሴሎም መጥቶ “ንጉሥ ሆይ፤ ለዘለዓለም ንገሥ፤ ንጉሥ ሆይ፤ ለዘለዓለም ንገሥ” አለው።


ስለዚህ የዳዊት ወዳጅ ሑሻይ ልክ አቤሴሎም ኢየሩሳሌም በገባበት ሰዓት ወደ ከተማዋ ደረሰ።


“አብርሃም በእግዚአብሔር አመነ፤ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት” የሚለው የመጽሐፍ ቃል ተፈጸመ፤ እርሱም የእግዚአብሔር ወዳጅ ተባለ።


ከደቀ መዛሙርቱም ኢየሱስ ይወደው የነበረው አንዱ በኢየሱስ ደረት ላይ ተጠጋ፤


የልብን ንጽሕናን የሚወድና ንግግሩ ለዛ ያለው ሰው፥ ንጉሥ ወዳጁ ይሆናል።


ሰሎሞን በመላው እስራኤል ዐሥራ ሁለት የክፍላተ ሀገር ገዢዎችን ሾመ፤ የእነርሱም ተግባር ከየግዛታቸው ለንጉሡና ለንጉሡ ቤተሰብ ቀለብ የሚሆነውን ነገር ሁሉ ማቅረብ ነበር፤ እያንዳንዳቸውም በዓመት ውስጥ ለአንድ ወር ቀለብ የማቅረብ ግዴታ ነበረባቸው።


እንዲሁም የያኢር ሰው ዒራ የዳዊት ካህን ነበር።


ጌታ ሕፃኑን ስለ ወደደም ስሙ ይዲድያ ተብሎ እንዲጠራ በነቢዩ በናታን በኩል ቃል ላከ።


የዮዳሔ ልጅ በናያ የከሪታውያንና የፈሊታውያን አለቃ ሲሆን፥ የዳዊት ወንዶች ልጆች ደግሞ አማካሪዎች ነበሩ።


ነቢዩን ናታንን፥ “እነሆ፤ እኔ ከዝግባ በተሠራ ቤተ መንግሥት ውስጥ እኖራለሁ፤ የእግዚአብሔር ታቦት ግን በድንኳን ውስጥ ይኖራል” አለው።


አሒሻር የተባለው፦ የቤተ መንግሥት አገልጋዮች ኀላፊ፤ አዶኒራም የተባለው የዓብዳ ልጅ፦ የግዳጅ ሥራ ተቆጣጣሪ ነበሩ።


በኢየሩሳሌም የተወለዱለትም ልጆች ሻሙዓ፥ ሾባብ፥ ናታን፥ ሰሎሞን፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች