ንጉሡም፥ “በዚህ ሁሉ የኢዮአብ እጅ የለበትምን?” ሲል ጠየቃት። ሴቲቱም መልሳ እንዲህ አለች፤ “ንጉሥ ጌታዬ ሆይ በሕያው ነፍስህ እምላለሁ፤ ንጉሥ ጌታዬ ከተናገረው ሁሉ ወደ ቀኝም ወደ ግራም የሚል ማንም የለም። ይህን እንድናገር ያዘዘኝና ይህም ሁሉ ቃል በእኔ በአገልጋይህ አፍ ያደረገው አገልጋይህ ኢዮአብ ነው።
2 ሳሙኤል 14:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ወደ ንጉሡ ሂጂ፤ እንዲህም በዪው።” ከዚያም ኢዮአብ መናገር ያለባትን ነገር ነገራት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ወደ ንጉሡ ሄደሽ እንዲህ በዪው።” ከዚያም ኢዮአብ የምትናገራቸውን ቃላት ነገራት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም በኋላ ወደ ንጉሡ ቀርበሽ እኔ የምነግርሽን ንገሪው” አላት፤ ከዚህ በኋላ እርስዋ ልትናገረው የሚገባትን ሁሉ ኢዮአብ ነገራት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ንጉሡም ገብተሽ እንዲህ ያለውን ቃል ንገሪው” አላት፤ ኢዮአብም ቃሉን በእርስዋ አፍ አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ንጉሡም ገብተሽ እንዲህ ያለውን ቃል ንገሪው አላት፥ ኢዮአብም ቃሉን በእርስዋ አፍ አደረገ። |
ንጉሡም፥ “በዚህ ሁሉ የኢዮአብ እጅ የለበትምን?” ሲል ጠየቃት። ሴቲቱም መልሳ እንዲህ አለች፤ “ንጉሥ ጌታዬ ሆይ በሕያው ነፍስህ እምላለሁ፤ ንጉሥ ጌታዬ ከተናገረው ሁሉ ወደ ቀኝም ወደ ግራም የሚል ማንም የለም። ይህን እንድናገር ያዘዘኝና ይህም ሁሉ ቃል በእኔ በአገልጋይህ አፍ ያደረገው አገልጋይህ ኢዮአብ ነው።
በካሲፍያ ስፍራ አለቃ ወደ ሆነው ወደ ኢዶ ላክኋቸው፥ ለአምላካችን ቤት አገልጋዮችን እንዲያመጡልን በካሲፍያ ስፍራ ለሚኖሩት ለኢዶና ለወንድሞቹ ለቤተ መቅደስ አገልጋዮች ምን የሚነግሩአቸውን አስታወቅኳቸው።
ከእነርሱ ጋር ያለው ቃል ኪዳኔ ይህ ነው ይላል ጌታ፤ በአንተ ላይ ያለው መንፈሴ በአፍህም ውስጥ ያደረግሁት ቃሌ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለዓለም ድረስ ከአፍህ፥ ከዘርህም አፍ፥ ከዘር ዘርህም አፍ አይለይም፥ ይላል ጌታ።