ኢሳይያስ 51:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)16 ሰማያትን እንድዘረጋ ምድርንም እንድመሠርት፥ ጽዮንንም፦ “አንቺ ሕዝቤ ነሽ” እንድል ቃሌን በአፍህ አድርጌአለሁ፥ በእጄም ጥላ ጋርጄሃለሁ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም16 ቃሌን በአፍህ አኖርሁ፤ በእጄ ጥላ ጋረድሁህ፤ ሰማያትን በስፍራቸው ያስቀመጥሁ፣ ምድርን የመሠረትሁ፣ ጽዮንንም፣ ‘አንቺ ሕዝቤ ነሽ’ ያልሁ እኔ ነኝ።” ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም16 ቃሌን በአንደበትሽ አሳድራለሁ፤ አንቺንም በእጄ ጥላ ሥር እጋርድሻለሁ፤ ሰማያትን የዘረጋሁ፥ ምድርንም የመሠረትኩ እኔ ነኝ፤ ጽዮንንም ‘አንቺ ሕዝቤ ነሽ’ እላታለሁ።” ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)16 ቃሌን በአፍሽ አደርጋለሁ፤ ሰማይን በዘረጋሁበትና ምድርን በመሠረትሁበት በእጄ ጥላ እጋርድሻለሁ፤ ጽዮንንም አንቺ ሕዝቤ ነሽ እላታለሁ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)16 ሰማያትን እዘረጋ ዘንድ ምድርንም እመሠርት ዘንድ፥ ጽዮንንም፦ አንቺ ሕዝቤ ነሽ እል ዘንድ ቃሌን በአፍህ አድርጌአለሁ፥ በእጄም ጥላ ጋርጄሃለሁ። ምዕራፉን ተመልከት |