ከብዙ ጊዜ በኋላ የሹዓ ልጅ፥ የይሁዳ ሚስት ሞተች። ይሁዳ ከሐዘኑ ከተጽናና በኋላ ከዓዶላማዊው ከሒራ ጋር የበጎቹን ጠጉር የሚሸልቱ ሰዎች ወዳሉበት ወደ ተምና ሄደ።
2 ሳሙኤል 13:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ንጉሡም ሄዶ፥ “እነሆ፤ አገልጋይህ በጎቹን ይሸልታል፤ ንጉሡና ሹማምንቱ ፈቃዳቸው ሆኖ እባክህ ይገኙልኝ?” ሲል ጠየቀው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አቤሴሎምም ወደ ንጉሡ ሄዶ፣ “እነሆ፤ ባሪያህ በጎቹን እየሸለተ ነው፤ ታዲያ ንጉሡና ሹማምቱ ፈቃዳቸው ሆኖ እባክህ ይገኙልኝ?” ሲል ጠየቀው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ ንጉሥ ዳዊትም ሄዶ “ንጉሥ ሆይ! በጎቼን እየሸለትሁ ነው፤ ስለዚህ አንተና መኳንንትህ መጥታችሁ የግብዣው ተካፋዮች እንድትሆኑልኝ ትፈቅዳለህን?” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤሴሎምም ወደ ንጉሡ መጥቶ፥ “እነሆ፥ አገልጋይህ በጎቹን ያሸልታል፤ ንጉሡ ከአገልጋይህ ጋር ይሂድ፤ አገልጋዮቹም ይሂዱ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቤሴሎምም ወደ ንጉሡ መጥቶ፦ እነሆ፥ ባሪያህ በጎቹን ያሸልታል፥ ንጉሡና ሎሌዎቹ ከባሪያህ ጋር ይሂዱ አለው። |
ከብዙ ጊዜ በኋላ የሹዓ ልጅ፥ የይሁዳ ሚስት ሞተች። ይሁዳ ከሐዘኑ ከተጽናና በኋላ ከዓዶላማዊው ከሒራ ጋር የበጎቹን ጠጉር የሚሸልቱ ሰዎች ወዳሉበት ወደ ተምና ሄደ።
ከሁለት ዓመት በኋላ አቤሴሎም በኤፍሬም አቅራቢያ ባለችው በበዓለ ሐጾር ከተማ በጎቹን ይሸልት ነበር፤ ከዚያም የንጉሡን ወንዶች ልጆች ሁሉ በዚያ እንዲገኙለት አቤሴሎም ጋበዛቸው።
ንጉሡም አቤሴሎምን፥ “ልጄ ሆይ፥ ሸክም ስለምናበዛብህ ሁላችንም መሄድ የለብንም” ሲል መለሰለት። አቤሴሎም አጥብቆ ቢለምነውም ንጉሡ መሄድ አልፈለገም፤ ነገር ግን መርቆ አሰናበተው።
በዚህ ጊዜ በጎች እንደምትሸልት ሰምቻለሁ፤ እረኞችህ ከእኛ ጋር በነበሩበት ጊዜ፥ ያደረስንባቸው ጉዳት የለም፤ ቀርሜሎስ በነበሩበት ጊዜ ሁሉ፥ የጠፋባቸው አንዳች ነገር አልነበረም።