2 ሳሙኤል 1:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እስራኤል ሆይ፤ ክብርህ በኰረብቶችህ ላይ ተወግቶ ሞቷል! ኀያላኑ እንዴት ወደቁ! አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እስራኤል ሆይ፤ ክብርህ በኰረብቶችህ ላይ ተወግቶ ሞቷል፤ ኀያላኑ እንዴት እንደዚህ ይውደቁ! አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እስራኤል ሆይ! ያንተ ጀግና በተራሮች ላይ ተገድሎ ወደቀ! ኀያላኑ እንዴት ወደቁ! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እስራኤል ሆይ፥ ለሞቱትና ለተገደሉት ሐውልት ትከል፤ ኀያላን እንዴት ወደቁ! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤል ክብር በኮረብቶች ላይ ተወግቶ ሞተ፥ ኃያላን እንዴት ወደቁ! |
አሌፍ። ጌታ በቁጣው የጽዮንን ሴት ልጅ እንደምን አደመናት! የእስራኤልን ውበት ከሰማይ ወደ ምድር ጣለ፥ በቁጣውም ቀን የእግሩን መረገጫ አላሰበም።
እኔም ለእርድ የሚሆኑትን በጎች፥ የመንጋውን ችግረኞች ጠበቅሁ። ሁለት በትሮችንም ወሰድሁ፤ የአንዲቱን ስም “ደስታ” የሁለተኛይቱንም ስም “አንድነት” ብዬ ጠራሁ፤ መንጋውንም አሰማራሁ።