ሆኖም ከትዕቢቱ ምንም አልታቀበም፤ ሁልጊዜ በትዕቢቱ ተሞልቶ በአይሁዳውያን ላይ በንዴት ይቃጠል ነበር፤ ጉዞውም እንዲፋጠን ያዝዝ ነበር። ከሚሮጠው ሠረገላ ክፉና ወደቀና የአካሉ መገጣጠሚያዎች ከቦታቸው ተዛነፉ፤