ጰጠሎሜዮስ የጳጥርኩልን ልጅ ኒቃኖርን በደረጀ ከንጉሡ ወዳጆች ጋር የሚቆጠረውን የአይሁድን ዘር እንዲደመሰስ ከተለያዩ የዓለም አካባቢዎች ከሃያ ሺህ በማያንሱ ወታደሮች ላይ አለቃ አድርጐ ላከው። በጦር ስልት የታወቀውን ተዋጊ ሰው ጐርጊያስንም ጨመረለት።