ይሁዳ መቃቢስ የወታደሮቹን መቃረብ፥ ልዩ ልዩ የጦር መሣሪያዎቻቸውን ዝግጅትና የዝሆኖቹን አስፈሪነት ተመለከተ። እጆቹን ወደ ሰማይ ዘርግቶ ታምራትን ለሚያደርገው አምላክ ልመና አቀረበ፤ ምክንያቱም ማሸነፍ የሚቻለው በጦር መሣሪያ አለመሆኑንና ድል የሚገኘው በአምላክ ውሳኔና እሱ ድልን ለሚገባቸው ሰዎች ሲሰጥ ብቻ መሆኑን አወቀ።