ይሁዳ በተናገራቸው መልካምና በጀግነት በሚያነሣሡ፥ ለወጣቶችም በወንድነት ለመዋጋት ብርታት የሚሰጡ ቃላት ተጠናክረው አይሁዳውያን በሠፈር መቆየት ሳይሆን በድፈረት ወደ ጦርነት ለመሄድና በኃይል ለመዋጋት ቆረጡ፤ ምክንያቱም ከተማቸው፥ ሃይማኖታቸውና ቤተ መቅደሳቸው በአደጋ ላይ በመገኘታቸው ነው።