የጉዳዮቹ ፈጻሚ የሆነው የእርሱ መምህር ሊስያስም ከእርሱ ጋር መሆኑን ሰሙ። የአረማውያን (የግሪካውያን) ጦር ቁጥሩ መቶ ዐሥር ሺህ እግረኛ ጦር፥ አምስት ሺህ ሦስት መቶ ፈረሰኛ ጦር፥ ሃያ ሁለት ዝሆኖችና መቶ ባለ ማጨድ ሠረገላዎች ነበር።