በይሁዳ የሚመራው ጦር ሠራዊት በመጀመሪያ ብቅ ባለ ጊዜ ጠላት ተሸበረ፤ ሁሉን የሚያይ አምላክ በግልጽ ፍርሃት አሳደረባቸው፤ በያሉበት ሸሹ፤ እርስ በርሳቸው ተቋሰሉ፥ በጐራዴም (በሰይፍም) አንዱ ሌላውን ይወጋ ነበር።