በፊት ጊዜ አይሁዳውያን አሸንፈውት የነበረ ጢሞቴዎስ ብዙ የውጭ አገር ሰዎች አሰልፎ፥ ከእስያ የመጡ ብዙ ፈረሶች ሰብስቦ፥ በጦር መሣሪያ ሰዎቹን ለማንበርከክ አስቦ ወደ ይሁዳ ምድር መጣ።