በዚያኑ ጊዜ በደንብ የተዘጋጁትን ምሽጐች ይዘው የነበሩ ኤዱማውያን ይሁዳውያንን ያስቸግሩ ነበር፤ ከኢየሩሳሌም ሸፍተው የሄዱትን ሰዎች ተቀብለው ጦርነትን ያነሣሡ ነበር።