2 ዜና መዋዕል 32:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጦር አዛዦቹንም በሕዝቡ ላይ ሾሞ፥ ሁሉንም በከተማይቱ በር ወዳለው አደባባይ ሰበሰበ፥ እንዲህም ብሎ አበረታታቸው፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጦር መኰንኖችንም በሕዝቡ ላይ ሾሞ በከተማዪቱ በር አደባባይ ላይ በፊቱ ከሰበሰበ በኋላ፣ እንዲህ ሲል አበረታታቸው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የከተማይቱ ነዋሪዎች የሆኑ ወንዶች ሁሉ፥ በጦር መኰንኖች ሥልጣን ሥር እንዲሆኑ አድርጎ፥ በከተማይቱ ቅጽር በር አጠገብ በሚገኘው ገላጣ አደባባይ ላይ ሰበሰባቸው፤ እንዲህም በማለት አበረታታቸው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጦር አለቆቹንም በሕዝቡ ላይ ሾመ፤ ሁሉንም በሸለቆው በኩል ባለው በከተማዪቱ በር አደባባይ ወደ እርሱ ሰበሰበ፤ እንዲህም ብሎ ልባቸውን አጸና፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጦር አለቆቹንም በሕዝቡ ላይ ሾሞ፤ ሁሉንም በከተማይቱ በር ወዳለው አደባባይ ሰብስቦ |
ሕዝቅያስም በጌታ አገልግሎት አስተዋዮች የነበሩትን ሌዋውያን ሁሉ ያበረታታ ነበር። የአንድነትንም መሥዋዕት እያቀረቡ፥ የአባቶቻቸውንም አምላክ እያመሰገኑ ለሰባት ቀን ለበዓሉ የተዘጋጀውን ማዕድ በሉ።
በሦስት ቀን ውስጥ በዘጠነኛው ወር ከወሩም በሀያኛው ቀን የይሁዳና የብንያም ሰዎች ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ። ሕዝቡም ሁሉ ስለዚህ ነገርና ስለ ታላቁ ዝናብ እየተንቀጠቀጡ በእግዚአብሔር ቤት ፊት ባለው አደባባይ ተቀመጡ።
ሕዝቡም ወጥተው አመጡ፥ እያንዳንዱ በቤቱ ሰገነት ላይ፥ በየግቢያቸው፥ በእግዚአብሔር ቤት ግቢ፥ በ “ውኃ በር” አደባባይና በኤፍሬም በር አደባባይ ላይ ዳሶችን ሠሩ።
ለኢየሩሳሌም ልብ ተናገሩ፤ የተቀጠረችበት ወራት እንደ ተፈጸመ፥ ኃጢአትዋም እንደ ተሰረየ፥ ከጌታም እጅ ስለ ኃጢአትዋ ሁሉ ሁለት እጥፍ እንደ ተቀበለች ወደ እርሷ ጩኹ።