2 ዜና መዋዕል 32:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 ንጉሥ ሕዝቅያስም ራሱን ለሥራ ጽኑ አደረገ፥ የፈረሰውንም ቅጥር ሁሉ ጠገነ፥ በላዩም ግንብ ሠራበት፥ ከእርሱም በስተ ውጭ ሌላ ቅጥር ሠራ፤ በዳዊትም ከተማ ያለችውን ሚሎን አጠነከረ፤ ብዙም የጦር መሣሪያና ጋሻ ሠራ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም5 ከዚህ በኋላም ንጉሡ ጠንክሮ በመሥራት፣ ከቅጥሩ የፈራረሱትን ሁሉ ጠገነ፤ በላዩም ማማ ሠራበት፤ በውጭ በኩልም ሌላ ቅጥር በመገንባት የዳዊትን ከተማ ድጋፍ እርከን አጠናከረ፤ እንደዚሁም ብዙ የጦር መሣሪያዎችንና ጋሻዎችን ሠራ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 ንጉሥ ሕዝቅያስም ቅጽሮችን ጠግኖ በላያቸው ላይ የመቈጣጣሪያ ግንቦችን በመሥራትና ከውጪም በኩል ቅጽሮችን በመገንባት የከተማይቱን መከላከያዎች አጠናከረ፤ በተጨማሪም ከጥንታዊት ኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ በኩል በሚገኘው በተደለደለው ቦታ ላይ የተሠሩትን መከላከያዎች አደሰ፤ ብዙ ጦርና ጋሻም ሠራ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 ሕዝቅያስም ሰውነቱን አጽናና፤ የፈረሰውንም ቅጥር ሁሉ ጠገነ፤ በላዩም ግንብ ሠራበት፤ ከእርሱም በስተውጭ ሌላ ቅጥር ሠራ፤ ወደ ዳዊትም ከተማ የሚያወጣውን በር አጠነከረ፤ ብዙም መሣሪያና ጋሻ አዘጋጀ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 ሰውነቱንም አጸናና፥ የፈረሰውንም ቅጥር ሁሉ ጠገነ፤ በላዩም ግንብ ሠራበት፤ ከእርሱም በስተ ውጭ ሌላ ቅጥር ሠራ፤ በዳዊትም ከተማ ያለችውን ሚሎን አጠነከረ፤ ብዙም መሣሪያና ጋሻ ሠራ። ምዕራፉን ተመልከት |