Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢሳይያስ 40:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ለኢየሩሳሌም ልብ ተናገሩ፤ የተቀጠረችበት ወራት እንደ ተፈጸመ፥ ኃጢአትዋም እንደ ተሰረየ፥ ከጌታም እጅ ስለ ኃጢአትዋ ሁሉ ሁለት እጥፍ እንደ ተቀበለች ወደ እርሷ ጩኹ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ለኢየሩሳሌም አለዝባችሁ ንገሯት፤ ዐውጁላትም፤ በባርነት ያገለገለችበት ዘመን አብቅቷል፤ የኀጢአቷም ዋጋ ተከፍሏል፤ ስለ ኀጢአቷ ሁሉ ከእግዚአብሔር እጅ ሁለት ዕጥፍ ተቀብላለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 የባርነት ጊዜዋ እንዳለቀ፥ ለፈጸመችው ኃጢአት ሁሉ ከእግዚአብሔር ዘንድ እጥፍ ቅጣት እንደ ተቀበለችና ኃጢአትዋም ይቅር እንደ ተባለላት ለኢየሩሳሌም በለሰለሰ አነጋገር ንገሯት።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ካህ​ናት ሆይ፥ ለኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ልቧ የሚ​ገባ ነገ​ርን ተና​ገሩ፤ ውር​ደቷ እንደ ተፈ​ጸመ፥ ኀጢ​አ​ቷም እንደ ተሰ​ረየ፥ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጅ ስለ ኀጢ​አቷ ሁሉ ሁለት እጥፍ እንደ ተቀ​በ​ለች አጽ​ና​ኑ​አት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ለኢየሩሳሌም ልብ ተናገሩ፥ የተቀጠረችበት ወራት እንደ ተፈጸመ፥ ኃጢአትዋም እንደ ተሰረየ፥ ከእግዚአብሔርም እጅ ስለ ኃጢአትዋ ሁሉ ሁለት እጥፍ እንደ ተቀበለች ወደ እርስዋ ጩኹ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢሳይያስ 40:2
54 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ነፍሱም በያዕቆብ ልጅ በዲና ፍቅር ተነደፈች፥ ልጅቱንም አፈቀራት፥ እርሷንም በአፍቅሮት አናገራት።


ሕዝቅያስም በጌታ አገልግሎት አስተዋዮች የነበሩትን ሌዋውያን ሁሉ ያበረታታ ነበር። የአንድነትንም መሥዋዕት እያቀረቡ፥ የአባቶቻቸውንም አምላክ እያመሰገኑ ለሰባት ቀን ለበዓሉ የተዘጋጀውን ማዕድ በሉ።


የዳዊት ትምህርት። መተላለፉ ይቅር የተባለችለት፥ ኃጢአቱም የተከደነችለት ምስጉን ነው።


የሕዝብህን በደል አስቀረህ፥ ኃጢአታቸውንም ሁሉ ይቅር አልክ።


የሰረቀው በሬ ወይም አህያ ወይም በግ ቢሆንና በሕይወት ሳለ በእጁ ቢገኝ፥ የሰረቀውን ሁለት እጥፍ አድርጎ ይክፈል።


ለማልቀስ ጊዜ አለው፥ ለመሳቅም ጊዜ አለው፥ ዋይ ለማለት ጊዜ አለው፥ ለመዝፈንም ጊዜ አለው፥


በዚያን ቀን እንዲህ ትላለህ፤ “ጌታ ሆይ፤ ቀድሞ ተቈጥተኸኝ ነበር፤ አሁን ግን ከቁጣህ ተመለስህ፤ ደግሞም አጽናንተኸኛልና እወድስሃለሁ።


በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ጌታ ከኀዘንህና ከመከራህ ከተገዛህለትም ከጽኑ ባርነት ያሳርፍሃል።


ስለዚህም የማምለኪያ ዐፀዶችና የፀሐይ ምስሎች ዳግመኛ እንዳይነሡ የመሠዊያውን ድንጋይ ሁሉ እንደ ደቀቀ እንደ ኖራ ድንጋይ ባደረገ ጊዜ፥ እንዲሁ የያዕቆብ በደል ይሰረያል፥ ይህም ኃጢአትን የማስወገድ ፍሬ ነው።


በዚያም የሚኖር ማንም፦ “ታምሜአለሁ” አይልም፤ በእርሷም ለሚኖሩ ሰዎች በደላቸው ይቅር ይባልላቸዋል።


ፈሪ ልብ ላላቸው፦ “እነሆ፥ አምላካችሁ ለበቀል፥ ብድራት ለመመለስ ይመጣል፤ መጥቶም ያድናችኋልና በርቱ፥ አትፍሩ!” በሉአቸው።


መተላለፍህን፦ ስለ እኔ ስል የምደመስስ እኔ ነኝ፤ ኃጢአትህንም አላስብም።


መተላለፍህን እንደ ደመና፥ ኃጢአትህንም እንደ ጭጋግ ደምስሼአለሁ፤ ተቤዥቼሃለሁና ወደ እኔ ተመለስ።


ጌታ ግን እንዲህ ይላል፦ ከአንቺ ጋር የሚጣሉትን እጣላቸዋለሁ፥ ልጆችሽንም አድናለሁና፥ በኃያላን የተማረኩ እንኳን ይወሰዳሉ፥ የጨካኞች ብዝበዛም ቢሆን ያመልጣል።


ከጌታ እጅ የቁጣውን ጽዋ የጠጣሽ ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ንቂ፥ ንቂ! ቁሚ፤ የሚያንገደግድን ዋንጫ ጠጥተሻል ጨልጠሽውማል።


እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፤ በእርሱም ቁስል እኛ ተፈወስን።


እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ፤ ጌታም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ።


እነሆ፥ ጥቃት ቢደርስብሽ፥ ከእኔ ዘንድ ግን አይሆንም፤ በአንቺም ላይ የሚነሡ ሁሉ ከአንቺ የተነሣ ይወድቃሉ።


በአንቺ ላይ የተሠራ መሣሪያ ሁሉ አይከናወንም፤ በፍርድም የሚነሣብሽን ምላስ ሁሉ ትፈርጂበታለሽ። የጌታ አገልጋዮች ርስት ይህ ነው፥ ጽድቃቸውም ከእኔ ዘንድ ነው፥ ይላል ጌታ።


ክፉ ሰው መንገዱን በደለኛም አሳቡን ይተው፤ ወደ ጌታም ይመለስ እርሱም ይምረዋል፤ ይቅርታውም ብዙ ነውና ወደ አምላካችን ይመለስ።


አፌንም በእሳቱ ነክቶ፤ “እነሆ፤ ይህ ከንፈሮችህን ነክቶአል፤ በደልህ ተወግዶልሃል፤ ኃጢአትህም ተሰርዮልሃል” አለኝ።


በኀፍረታችሁ ፈንታ ሁለት እጥፍ ይሆንላችኋል፤ በውርደታችሁም ፋንታ ዕድል ፋንታችሁ ደስ ይለዋል፤ ስለዚህ የምድራቸውን ሁለት እጥፍ ይገዛሉ፥ የዘለዓለምም ደስታ ይሆንላቸዋል።


እናት ልጇን እንደምታጽናና እንዲሁ አጽናናችኋለሁ፥ በኢየሩሳሌምም ውስጥ ትጽናናላችሁ።


ምድሬንም በተጠሉ ጣዖቶቻቸው ሬሳዎች አርክሰዋልና፥ ርስቴንም አስጸያፊ በሆኑ ነገሮች ሞልተዋልና አስቀድሜ የበደላቸውንና የኃጢአታቸውን ዕዳ ሁለት እጥፍ እከፍላቸዋለሁ።”


አሳዳጆቼ ይፈሩ፥ እኔ ግን አልፈር፤ እነርሱ ይደንግጡ፥ እኔ ግን አልደንግጥ፤ ክፉንም ቀን አምጣባቸው፥ በሁለት እጥፍ ጥፋት አጥፋቸው።


ለእናንተ የማስበውን አሳብ እኔ ጠንቅቄ አውቃለሁ፥ ይላል ጌታ፤ ለወደፊት የሠመረ ጊዜና ተስፋ ልሰጣችሁ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም።


ጌታ ጽድቃችንን በግልጥ አውጥቶአል፤ ኑ፥ በጽዮን የአምላካችንን የጌታን ሥራ እንናገር።


ታው። የጽዮን ልጅ ሆይ፥ የበደልሽ ቅጣት ተፈጸመ፥ ከእንግዲህ ወዲህ አያስማርክሽም። የኤዶምያስ ልጅ ሆይ፥ በደልሽን ይቀጣል፥ ኃጢአትሽን ይገልጣል።


በአንቺ ላይ ያለውን መዓቴን አቆማለሁ፥ ቅንዓቴም ከአንቺ ይርቃል፥ እኔም ዝም እላለሁ፥ ከእንግዲህም አልቆጣም።


እርሷም፦ “ውሽሞቼ ለእኔ የሰጡኝ ዋጋዬ ይህ ነው” ያለችውን ወይንዋንና በለስዋን አጠፋለሁ፤ ዱርም አደርገዋለሁ፥ የምድረ በዳም አራዊት ይበሉታል።


ስለዚህ፥ እነሆ፥ አባብላታለሁ፥ ወደ ምድረ በዳም አመጣታለሁ፥ ለልብዋም እናገራለሁ።


ራእዩ ገና እስከ ተወሰነው ጊዜ ነው፥ ወደ ፍጻሜውም ይፈጥናል፥ እርሱም አይዋሽም፤ ቢዘገይም በእርግጥ ይመጣልና ጠብቀው፤ አይዘገይም።


ጌታ ቅጣትሽን አስወግዷል፥ ጠላትሽንም አጥፍቷል፤ የእስራኤል ንጉሥ ጌታ በመካከልሽ አለ፥ ከእንግዲህም ወዲህ ክፉ ነገርን አትፈሪም።


ጌታም መልሶ ከእኔ ጋር ይነጋገር ለነበረው መልአክ በመልካምና በሚያጽናና ቃል ተናገረው።


እኔ ብዙም ሳልቆጣቸው እነርሱ ክፋትን ስላገዙት፥ በምቾት በሚኖሩት አሕዛብ ላይ እጅግ ተቈጥቻለሁ።


እናንተ በተስፋ የምትኖሩ እስረኞች ሆይ፥ ወደ ጽኑ አምባ ተመለሱ፤ ሁለት እጥፍ አድርጌ እንደምመልስልሽ ዛሬ እነግርሻለሁ።


እርሱም “አብ በገዛ ሥልጣኑያደረገውን ወራትንና ዘመናትን ታውቁ ዘንድ ለእናንተ አልተሰጣችሁም፤


የዘመኑ ሙላት በመጣ ጊዜ፥ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግ ሥር የተወለደውን ልጁን ላከ፤


እርሷ በሰጠችው መጠን መልሱላት፤ እንደ ሥራዋም ሁለት እጥፍ ደርቡባት፤ በቀላቀለችው ጽዋ ሁለት እጥፍ አድርጋችሁ ቀላቅሉባት፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች