1 ጢሞቴዎስ 5:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሮጊቶችን እንደ እናቶች፥ ወጣት ሴቶችን እንደ እኅቶች አድርገህ በፍጹም ንጽሕና ተመልከት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም አሮጊቶችን እንደ እናቶች፣ ወጣት ሴቶችን ደግሞ እንደ እኅቶች በፍጹም ንጽሕና አስተናግዳቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሮጊቶችን እንደ እናቶች አድርገህ ተመልከታቸው፤ እንዲሁም ወጣት ሴቶችን እንደ እኅቶች አድርገህ በፍጹም ንጽሕና ተመልከታቸው። |
በቀረውስ ወንድሞች ሆይ! እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ክቡር የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ንጹሕ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ፍቅር ያለበትን ነገር ሁሉ፥ ምስጉን የሆነውን ነገር ሁሉ፥ በጎነት ቢሆን ምስጋናም ቢሆን፥ እነዚህን አስቡ፤