ከዚህም በላይ ደግሞ የአምላኬን ቤት ስለወደድሁ፥ ለመቅደሱ ካዘጋጀሁት ሁሉ ሌላ የግል ገንዘቤ የሚሆን ወርቅና ብር አለኝና ለአምላኬ ቤት ሰጥቼዋለሁ።
1 ሳሙኤል 9:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተገኝተዋልና፥ ከሦስት ቀን በፊት ስለ ጠፉብህ አህዮች አትጨነቅ። የእስራኤል ምኞት ሁሉ ያዘነበለው ወደ ማን ነው? ወደ አንተና ወደ አባትህ ቤተሰብ ሁሉ አይደለምን?” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሦስት ቀን በፊት ስለ ጠፉብህ አህዮች አትጨነቅ፤ ተገኝተዋልና። የእስራኤል ምኞት ሁሉ ያዘነበለው ወደ አንተና ወደ አባትህ ቤተ ሰብ ሁሉ አይደለምን?” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሦስት ቀን በፊት የጠፉት አህዮችህ ተገኝተዋልና ስለ እነርሱ አትጨነቅ፤ ነገር ግን የእስራኤል ሕዝብ ምኞት ማንን ለማግኘት ይመስልሃል? እነርሱ የሚፈልጉት አንተንና የአባትህን ቤተሰብ አይደለምን?” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሦስት ቀንም በፊት የጠፉ አህዮችህ ተገኝተዋልና ልብህን አታስጨንቀው። የእስራኤል መልካም ምኞት ለማን ነው? ለአንተና ለአባትህ ቤት አይደለምን?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሦስት ቀንም በፊት የጠፉ አህዮችህ ተገኝተዋልና ልብህን አትጣልባቸው። የእስራኤልም ምኞት ለማን ነው? ለአንተና ለአባትህ ቤት አይደለምን? አለው። |
ከዚህም በላይ ደግሞ የአምላኬን ቤት ስለወደድሁ፥ ለመቅደሱ ካዘጋጀሁት ሁሉ ሌላ የግል ገንዘቤ የሚሆን ወርቅና ብር አለኝና ለአምላኬ ቤት ሰጥቼዋለሁ።
ለመሞትም በምታጣጥርበት ጊዜ፥ በአጠገቧ የነበሩት ሴቶች፥ “አይዞሽ፤ ወንድ ልጅ ወልደሻልና በርቺ” አሏት። እርሷ ግን መልስ አልሰጠችም፤ ልብ ብላም አላዳመጠችም።
እነርሱም፥ “አንተ አርጅተሃል፤ ልጆችህም በመንገድህ አይሄዱም፤ ስለዚህ ሌሎች ሕዝቦች እንደሚያደርጉት ሁሉ የሚመራን ንጉሥ አንግሥልን” አሉት።
ሳሙኤልም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “ባለ ራእዩ እኔ ነኝ፤ ዛሬ ከእኔ ጋር ስለምትበሉ፤ ከፊቴ ቀድማችሁ ወደ ማምለኪያው ኰረብታ ውጡ፤ ነገ ጠዋት አሰናብትሃለሁ፤ በልብህ ያለውንም እነግርሃለሁ።
በዚያም ጊዜ የሳኦል አባት የቂስ አህዮች ጠፍተው ነበር፤ ቂስም ልጁን ሳኦልን፥ “ከአገልጋዮቹ መካከል አንዱን ይዘህ ሂድና አህዮቹን ፈልግ” አለው።