Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 4:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ለመሞትም በምታጣጥርበት ጊዜ፥ በአጠገቧ የነበሩት ሴቶች፥ “አይዞሽ፤ ወንድ ልጅ ወልደሻልና በርቺ” አሏት። እርሷ ግን መልስ አልሰጠችም፤ ልብ ብላም አላዳመጠችም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ለመሞትም በምታጣጥርበት ጊዜ፣ በአጠገቧ የነበሩት ሴቶች፣ “አይዞሽ፤ ወንድ ልጅ ወልደሻልና በርቺ” አሏት። እርሷ ግን መልስ አልሰጠችም፤ ልብ ብላም አላዳመጠችም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 እርስዋም ለመሞት በምታጣጥርበት ጊዜ በማዋለድ የምትረዳት ሴት “አይዞሽ በርቺ! ወንድ ልጅ ወልደሻል!” አለቻት፤ ነገር ግን አዳምጣ መልስ አልሰጠቻትም፤ አላተኰረችበትምም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ወደ ሞትም በቀ​ረ​በች ጊዜ በዙ​ሪ​ያዋ ያሉት ሴቶች “ወንድ ልጅ ወል​ደ​ሻ​ልና አት​ፍሪ” አሉ​አት። እር​ስዋ ግን አል​መ​ለ​ሰ​ች​ላ​ቸ​ውም፤ ልብ​ዋም አያ​ስ​ታ​ው​ስም ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ወደ ሞትም በቀረበች ጊዜ በዙሪያዋ ያሉት ሴቶች፦ ወንድ ልጅ ወልደሻልና አትፍሪ አሉአት። እርስዋ ግን አልመለሰችላቸውም፥ በልብዋም አላኖረችውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 4:20
5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከቤቴልም ተነሡ፥ ወደ ኤፍራታም ሊደርሱ ጥቂት ሲቀራቸው ራሔልን ምጥ ያዛት፥ በምጡም ተጨነቀች።


በቃሌ ወደ እግዚአብሔር ጮኽሁ፥ ቃሌም ወደ እግዚአብሔር ነው፥ እርሱም አደመጠኝ።


ሴት በምትወልድበት ጊዜ ወራትዋ ስለ ደረሰ ታዝናለች፤ ነገር ግን ሕፃን ከወለደች በኋላ፥ ሰው በዓለም ተወልዶአልና በደስታዋ ምክንያት መከራዋን ከቶውን አታስበውም።


በዚያን ጊዜ ምራቱ የፊንሐስ ሚስት፥ ነፍሰ ጡር ነበረች፤ የምትወልድበትም ጊዜ ተቃርቦ ነበር፥ የእግዚአብሔርን ታቦት መማረክ፥ የዐማቷንና የባሏንም መሞት በሰማች ጊዜ ምጡ ስለ ጠናባት ተንበርክካ ወለደች።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች